የኢ.ጨ.መ.ባ አዳዲስ ዜናዎች

የጨረራ ክስተቶችና አደጋዎች(Radiological incidents & Accident)

የጨረራ አደጋ ወይንም ራዴሽን አክሲደንት ስንል ባልተጠበቀ ሁኔታ ለአይዮን ፈጣሪ የጨረራ አመንጪ ቁሶች መጋለጥ ነው፡፡ ይህ አደጋ በተጨባጭ ወይንም ተጨባጭ ባልሆነ መልኩ ሊከሠት ይችላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የጨረራ ጠቀሜታዎች

ጨረራ በአይን የማይታይ በሞገድ ወይም በልዩ ልዩ ቅንጣጢቶች መልክ ከቦታ ቦታ የሚጓዝ ሃይል ነው፡፡ ጨረራ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መንገድ ልናገኘው እንችላለን፡፡

በዛሬው ጽሁፍ የሰው ሰራሽ ጨረራን ጠቀሜታን ለማስተዋወቅ እንሞክራለን፡፡ ጨረራ በአለማችን ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ቴክኖሎጅ ከመሆኑ የተነሳ የአገራት የታላቅነት ሚስጢር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ለዚህም የአሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ቻይና ፣ ሰሜን ኮሪያን ነባራዊ ሁነታ ማየት እንችላለን፡፡ ሀገራቱ የሚፈሩትና የሚከበሩበት ዋነኛው ሚስጢር የኑክሌር ሃይል አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ /FOOD IRRADIATION/

በጨረራ በመጠቀም ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ በጨረራ በመታገዝ የሚከናወን ሲሆን አላማው ጎጅ ባክቴሪያዎችን፣ ነፍሳትንና ፓራሳይቶችን ወይም ምግብ ወለድ በሽታዎችን በማስወገድ የምግብን ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ሂደት ምግብን ለጋማ ሬይ፣ ኤክስሬይና አክስሌሬትድ ኤሌክትሮንስ በማጋለጥ የማጨረር ሂደት ሲሆን በዚህ ቴክኖሎጅ የጨረረ ምግብ ሳይንሳዊ ይዘቱን ስለማይለወጥ የወትሮ ጠቀሜታው እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ባለስልጣኑ በሆስፒታሎችና ክሊኒኮች ላይ እርምጃ ወሰደ

የጨረራ መከላከያ ህግ ሳያከብሩ ሲሰሩ የተገኙ ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች የራጅ ክፍሎች እንዲታሸጉ ተደረገ፡፡ በ2008 በጀት አመት በመጀመሪያ ሩብ አመት የባለስልጣኑ የጨረራ መከላከያ መኮንኖች በአዲስ አበባ፣ ቡታጅራ፣ ሀዋሳና ሻሸመኔ በሚገኙ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች የጨረራ ህክምና ክፍሎች ላይ ባደረጉት ፍተሻ በሰውና አካባቢ ላይ የጨረራ ብክለት መኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎች ጥራት ማነስ፣ ያለፈቃድ መስራትና በወቅቱ ፈቃድ አለማሳደስ በህክምና ተቋማት ዘንድ በክፍተትነት የተለዩ ችግሮች ሆነዋል፡፡በዚሁ የቁጥጥር ሂደት ወቅት 7 የህክምና ተቋማት የራጅ አገልግሎት ክፍሎች እንዲታሸጉ የተደረገ ሲሆን ጉዳያቸው በህግ እንደሚታይም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ተግባራዊ መደረግ የሚገባቸው የጨረራ መከላከያ ዘዴዎች

በየአለምዓቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ባስቀመጠው እስታንደርድ መሠረት ማንኛውም ሰው ሊተገብራቸው የሚገባ 3 ዋና ዋና የጨረራ መከላከያ ዘዴዎች አሉ፡፡ እነዚህም

ተጨማሪ ያንብቡ

የጨረራ ህክምና መሳሪያዎች ላይ የንድፈሃሳብና የተግባር ስልጠና

ከየካቲት 2-6ቀን2007ዓ.ም በአለምአቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ ትብብር ለ15 የባለስልጣኑ የጨረራ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች በማሞግራፊና በሲቲስካን የጨረራ ህክምና መሳሪያዎች ላይ የንድፈሃሳብና የተግባር ስልጠና በዶር.ናዳ አባስ ተሰጠ፡፡የስልጠናው አለማ በሲቲና ማሞግራፊ ላይ ያለን ክፍተት በመሙላት የተሟላ የጨረራ ቁጥጥር ለማድረግ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ባለስልጣኑ ያስገነባውን ዘመናዊ የራዲዮአክቲቭ ዝቃጭ ማቀነባበሪያና ማከማቻ ማዕከል በይፋ አስመረቀ

ባባለስልጣኑ ያስገነባውን ዘመናዊ ማዕከል ጳጉሜ 01 ቀን 2006 በ.ኢ.ፌ.ድ.ረ.ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚኒስትር ወ/ሮ ደማቱ ሀምቢሳ ና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተመረቀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ባለሥልጣኑ ከጨረራ ደህንነትና ጥራት ፍተሻ አካላት ጋር የውል ስምምነት ፈረመ

በባለሥልጣኑ ስልጣን ተግባር መሰረት የተለያዩ የጨረራ አመንጪዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት ከሀገር ለማስወጣት፣ ለመጠቀም፣ ለመጓጓዝ ለማስተላለፍ ለማስወገድ ወዘተ.. ፈቃዶችን የሚሰጥ ተቋም ሲሆን የውል ስምምነት ከተለያዩ የጨረራ ደህንነት አገልግሎቶች የሚሰጡ የጨረራ ደህንነት ወይም የጤና ፊዚክስን በተመለከተ የማማከር ሥራ የሚያከናውኑ (Radiation Safety Assessments) የሚያከናውኑ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥር 01 2006 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

በተፈጥሮ ስለሚገኙ የጨረራ አመንጪ ቁሶች(NORM – Naturally Occurring Radioactive Materials)

ጨረራ አመንጪ ቁሶች ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ በተለያየ የአፈጣጠር አይነትና መጠን የሚገኙ ሲሆን ከምድር ውስጥ፣ በምድር ገጽ እና ከምድር ገጽ በላይ በጠጣር፣ በፈሳሽ እና በጋዝ መልክ ይገኛሉ፡፡

ረዢም መንፈቀ ህይወት ያላቸው እንደ ዩራኒዬም፣ ቶሪዬም እና ፖታሲዬም እንዲሁም የነሱ ውጤት(ውልድ) የሆኑት እንደ ራዲዬምና ራዶን የተባሉት በተፈጥሮ የሚገኙ ጨረራ አመንጪ ቁሶች ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ቁሶች በምድር አለት እና ከባቢ አየር ውስጥ ምንጊዜም ይኖራሉ፡፡ የሰው ልጅም ምንም እንኳ ከነዚሁ በተፈጥሮ ከሚገኙ ጨረራ አመንጪዎች ቢጋለጥም የጨረራ ውስድ መጠኑ በጤናው ላይ ጉዳት ሳያስከትልበት አብሯቸው ይኖራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የባለስልጣኑን የቁጥጥር መስፈርቶች

ተቋማት/ድርጅቶች አዲስ የራጅ አገልግሎት ለመስጠት የሚከተሉትን የባለስልጣኑን የቁጥጥር መስፈርቶች ሊያሟሉ ይገባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

የጨረራ ቪድዮ

የኢ.ጨ.መ.ባ 2005 ዶክመንተር ቪድዮ.


በማህበራዊ ድረገጻችን ይጎብኙንYour Feed back

Detail address