Latest News Latest News

MyDisplayNews


የጨረራ ሰራተኞች የውስድ መጠን (የዶዚ ሜትሪ) ንባብ ድግግሞሽ አፈፃፀም

28/06/2018
ማንኛውም የጨረራ ሰራተኛ የጨረራ ደህንነትና ክትትል አገልግሎት የማግኘትና የመጠቀም መብት ሲኖረው ባለፈቃዱ ለሰራተኞቹ አገልግሎቱን በተሟላ መልኩ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህነ አገልግሎት ከማቅረብና ሰራተኞቹ እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር ዶዝ ሜትሪ ወቅቱን ጠብቆ ማስነበብና ውጤቱን ለሰራተኞቹ ማሳወቅ እንዲሁም ተገቢውን መረጃ መያዝ ከባለፍቃዱ የሚጠበቁ ግዴታዎች ናቸው፡፡ የዶዚ ሜትር አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ዶዚ ሜትሪ የማስነበብ፣የተገኘውን ውጤት ለባለፈቃዱ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ወቅቱን ጠብቆ ማሳወቅና ተገቢውን መረጃ በአግባቡ መያዝ አለበት፡፡

The Need for Radiological Emergency Preparedness and Response

22/05/2018
Ethiopia have been using radioactive materials and Sources for some decades; Despite all the precautions that are taken in the design and operation of radiological facilities and the conduct of activities, there remains always a possibility that may lead to an emergency due to a failure or a misuse during the peaceful application of radioactive materials and sources in the fields of medical, industry, teaching and research facilities.

ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ጉዳቱና መከላከያው

08/05/2018
ልዕለ ሀምራዊ ጨረራ ጉዳቱና መከላከያው (በታደለ ነጋሽ) አዮን ፈጣሪ ካልሆኑት የጨረራ አይነት ምድብ ውስጥ የሚገኘውና ልእለ ሀምራዊ ጨረራ (Ultra Violate Radiation (UVR)) በመባል ለሚታወቀው ጨረራ ከመጠን በላይ ሰውነታችን ቢጋለጥ በአይንና ቆዳ ላይ ከቀላል አንስቶ እስከ ከፍተኛ ጉዳት ማለትም የአይንን እይታ እስከመከለል እና በቆዳ ላይ ካንሰር እስከማስከተል ድረስ ችሎታ አለው፡፡

Ethiopian Radiation Protection Authority (ERPA) has accomplished an international Assessment by IAEA.

01/01/2018
An international team of senior safety experts that comprised 9 senior regulatory experts from IAEA member state and 2 IAEA staff has conducted an Integrated Regulatory Review Service (IRRS) mission from 3 to 12 December 2017 which aimed to perform a peer review of Ethiopian National Regulatory Framework for Nuclear Radiation safety.

የቼርኖቤል ጦስ ክፍል-1

16/01/2018
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 26 ቀን 1986 ዓ.ም፡፡ በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አንድ ክፍል በነበረችው በዩክሬይን ውስጥ ቼርኖቤል በተባለ ቦታ ተቀራርበው ከሚገኙ 4 የኑክሌር ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ውስጥ በአንደኛው ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከሰተ፡፡ ይሄው ፍንዳታ የደረሰበት ጣቢያ ለጥገና ተብሎ ማመንጨት ከሚችለው ሀይል 10 በመቶ ብቻ ለጥገናው ስራ እየተጠቀመ ነበር፡፡ የተከሰተው ፍንዳታ ለአስር ቀናት ያክል የተለያዩ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ አደገኛ ጨረራ አመንጭ ቁሶች ራዲዮኑክላይዶች በአየር ላይ እንዲበተን እና እንዲቀላቀል ያስገደደ ነበር፡፡ ይሄው ክስተት ከፍተኛ የአየር ብክለት አስከተለ፡፡ ብክለቱም በዚያው አካባቢ ብቻ ሳይወሰን በነፋስ አጋዥነት አውሮፓን እና ሌሎች አካባቢዎችን አዳረሰ፡፡

የቼርኖቤል ጦስ ክፍል 2

22/01/2018
አዮዲን-131 የተባለው ጨረራ አመንጭ ቁስ ጨረራ የማመንጨት ችሎታው በግማሽ የሚቀንስበት መንፈቀ ህይወቱ 8 ቀናት የሆነው በእንቅርት ውስጥ የሚከማች ከሆነ በህጻናት ላይ የሚያስከትለው ችግር ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ቼርኖቤል ያስከተለውን ውጤት የተባበሩት መንግስታት ኤስ.ሲ.ኢ.ኤ.አር በ2000 አትሙ አውጥቶታል፡፡ ይሄው ሳይንሳዊ ፍተሻ እንደሚሳየው በአደጋው ወቅት ከተጋለጡት ውስጥ 1800 ለእንቅርት ካንሰር የተዳረጉ ህጻናት እንደሚገኙበት ያሳያል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ከፈጠረው በርካታ ጉዳቶች አንጻር ከፍተኛ ህመም ቢኖርም ለሞት የዳረገ አልነበረም፡፡ ከጦሱ ጋር በተገናኘም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘም ፡፡

Regional Training hosted

14/05/2015
Regional training that aimed to enhance the competence required for regulatory bodies was held form April 20-24,2015 here in Addis Ababa at Jupiter International Hotel .The training entitled 'Regional Training Course on organization Staffing and Competency of the Regulatory body' was organized by the Ethiopian Radiation Protection Authority in cooptation with the International Atomic Energy Agency (IAEA).

ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ /FOOD IRRADIATION/

14/05/2016
በጨረራ በመጠቀም ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ በጨረራ በመታገዝ የሚከናወን ሲሆን አላማው ጎጅ ባክቴሪያዎችን፣ ነፍሳትንና ፓራሳይቶችን ወይም ምግብ ወለድ በሽታዎችን በማስወገድ የምግብን ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ሂደት ምግብን ለጋማ ሬይ፣ ኤክስሬይና አክስሌሬትድ ኤሌክትሮንስ በማጋለጥ የማጨረር ሂደት ሲሆን በዚህ ቴክኖሎጅ የጨረረ ምግብ ሳይንሳዊ ይዘቱን ስለማይለወጥ የወትሮ ጠቀሜታው እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡

የጨረራ ክስተቶችና አደጋዎች(Radiological incidents & Accident)

28/12/2017
የጨረራ አደጋ ወይንም ራዴሽን አክሲደንት ስንል ባልተጠበቀ ሁኔታ ለአይዮን ፈጣሪ የጨረራ አመንጪ ቁሶች መጋለጥ ነው፡፡ ይህ አደጋ በተጨባጭ ወይንም ተጨባጭ ባልሆነ መልኩ ሊከሠት ይችላል፡፡

የጨረራ ጠቀሜታዎች

28/12/2017
ጨረራ በአይን የማይታይ በሞገድ ወይም በልዩ ልዩ ቅንጣጢቶች መልክ ከቦታ ቦታ የሚጓዝ ሃይል ነው፡፡ ጨረራ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መንገድ ልናገኘው እንችላለን፡፡ በዛሬው ጽሁፍ የሰው ሰራሽ ጨረራን ጠቀሜታን ለማስተዋወቅ እንሞክራለን፡፡ ጨረራ በአለማችን ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ቴክኖሎጅ ከመሆኑ የተነሳ የአገራት የታላቅነት ሚስጢር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ለዚህም የአሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ቻይና ፣ ሰሜን ኮሪያን ነባራዊ ሁነታ ማየት እንችላለን፡፡ ሀገራቱ የሚፈሩትና የሚከበሩበት ዋነኛው ሚስጢር የኑክሌር ሃይል አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡

Your feedback Your feedback

Suggestions

Your input is valuable to us. Please send us your suggestions.

This field is mandatory.
This field is mandatory.

Play to see ERPA video Play to see ERPA video

Workshop on Radiation Safety and Security conducted Workshop on Radiation Safety and Security conducted

A workshop organized by the National Nuclear Security Administration of U.S in cooperation with the Ethiopian Radiation Protection Authority was conducted at Hilton Hotel, Addis Ababa, from August 3 to 4, 2015. The workshop focused on the development of regulations that is a vital tool for the security of radioactive sources and nuclear facilities. Specific topics such as IAEA Code of conduct which basically provides guidance for developing policies laws and regulations to uphold the safety and security of radioactive sources, categorization of radioactive sources that helps maintain a high level of safety and security, IAEA Nuclear Security Series that serves as a guidance for establishing regulating requirements, regulatory development process that introduces a systematic process which helps make development of new security regulations more effective and efficient and principles that highlight effective regulation drafting were critically addressed in the workshop.

Read More

Menu Menu

የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን አጠቃላይ አወቃቀርና አሠራርን በተመለከተ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በተላኩ ከተለያዩ የዓለም ሀገራትና ኃላፊነት በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በታህሳስ 2017 እ.ኤ.አ አጠቃላይ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን የተደረገው ግምገማ ሪፖርት ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይገኛል፡፡