ጨረራ አመንጪ ቁሶች ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ በተለያየ የአፈጣጠር አይነትና መጠን የሚገኙ ሲሆን ከምድር ውስጥ፣ በምድር ገጽ እና ከምድር ገጽ በላይ በጠጣር፣ በፈሳሽ እና በጋዝ መልክ ይገኛሉ፡፡

ረዢም መንፈቀ ህይወት ያላቸው እንደ ዩራኒዬም፣ ቶሪዬም እና ፖታሲዬም እንዲሁም የነሱ ውጤት(ውልድ) የሆኑት እንደ ራዲዬምና ራዶን የተባሉት በተፈጥሮ የሚገኙ ጨረራ አመንጪ ቁሶች ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ቁሶች በምድር አለት እና ከባቢ አየር ውስጥ ምንጊዜም ይኖራሉ፡፡ የሰው ልጅም ምንም እንኳ ከነዚሁ በተፈጥሮ ከሚገኙ ጨረራ አመንጪዎች ቢጋለጥም የጨረራ ውስድ መጠኑ በጤናው ላይ ጉዳት ሳያስከትልበት አብሯቸው ይኖራል፡፡

እነኚህን ለመለየት እና ለማየት የተፈለገው በሰው ሰራሽ መንገድ የሚገኙ በመኖራቸው ምክኒያት ነው፡፡ ሆኖም የሰው ልጅ የጨረራ መጋለጥ ፈጽሞ እንዳይደርስበት ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

የሰው ልጅ ባመዛኙ ለነዚህ በተፈጥሮ ለሚገኙ የጨረራ አመንጭዎች መጋለጡ ባማካይ ሊጋለጥ ከሚገባው የጨረራ ውስድ መጠን የዘለለ ባለመሆኑ ለከፋ የጤና እና የደህንነት ችግር አልዳረገውም ፡፡ ይሁንና አንዳንድ ኢንዱስትሪዎች እነኝህኑ በተፈጥሮ የሚገኙ ጨረራ አመንጭዎችን በከፍተኛ መጠን ተጠቅሞ ዝቃጩን በተለያየ መልኩ(በጠጣር፣ በፈሳሽ እና በጋዝ ወዘተ) ወደ አካባቢው ስለሚለቅ በጊዜ ሂደት በሰው ልጅ እና በአካባቢው ላይ አደጋ የሚያስከትሉ መሆኑ ታውቋል፡፡

ይሁንና በጊዜ ሂደት እነኚህ ከየኢንደስትሪው የሚወገዱ በተፈጥሮ ስለሚገኙ የጨረራ አመንጪ ቁሶች ጉዳት የሚያደርሱ መሆናቸው በመለየቱ ክትትልና ቁጥጥር የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ሀገራት ኢንደስተሪዎች ቁጥጥሩ ያን ያህልም አይደለም፡፡ እንደምክኒያትም የራዲዮአክቲቭ ቁሶች ዝቃጭ ሆነው የሚታሰቡ በሌላው ጋር እንዳይደሉ ስለሚታሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ከኒውክሌር ኢንዱስትሪ የሚወጣ ዝቃጭ ለሌላ አገልግሎት ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደሌላ ኢንደስትሪም በህገወጥ መንገድ ይወሰዳል፡፡

የዩራኒየም ማዕድን ማምረት እና ተያያዥ ስራዎችን ሳይጨምር በተፈጥሮ የሚገኙ የጨረራ አመንጪ ቁሶች ከሚገኙባቸው ኢንደስትሪዎች ውስጥ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ የነዳጅ እና ጋዝ ማምረቻ ኢንዱስተሪ፣ ብረታብረት ማዕድን ማምረቻ እና ማቅለጫዎች አካባቢ፣ የተለያዩ አሸዋማ ማዕድናት እንደ ቲታኒዬም እና ዚርኮኒዬም ምርት ሂደት፣ ማዳበሪያ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፣ የህንጻ ዕቃዎች ማምረቻ አካባቢ፣ በመልሶ መጠቀም(Recycling) አካባቢ ወዘተ ይገኙበታል፡፡


የጨረራ ቪድዮ

የኢ.ጨ.መ.ባ 2005 ዶክመንተር ቪድዮ.


Your Feed back

Detail address