በጨረራ በመጠቀም ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ በጨረራ በመታገዝ የሚከናወን ሲሆን አላማው ጎጅ ባክቴሪያዎችን፣ ነፍሳትንና ፓራሳይቶችን ወይም ምግብ ወለድ በሽታዎችን በማስወገድ የምግብን ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ሂደት ምግብን ለጋማ ሬይ፣ ኤክስሬይና አክስሌሬትድ ኤሌክትሮንስ በማጋለጥ የማጨረር ሂደት ሲሆን በዚህ ቴክኖሎጅ የጨረረ ምግብ ሳይንሳዊ ይዘቱን ስለማይለወጥ የወትሮ ጠቀሜታው እንደተጠበቀ ይገኛል፡፡

ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጀ የተጀመረው በ1930 ዓ.ም በአሜሪካን ሀገር ሲሆን በ1963 ዓ.ም የአሜሪካን መንግስት በመጀመሪያ ከስንዴ ላይ ነፍሳትን ለማስወገድ ሲባል ስንዴን ማጨረርን እውቅና ሰጥቷል፡፡ ከዚያም ፍላጎቱ እያየለ በመምጣት ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ በስጋ ምርቶች፣ አታክልቶች፣ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎችና ሌሎች ምግቦች ላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ባደረገው ጥናትም ይህ ቴክኖሎጅ የምግቦችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊና በምግቦች ላይ ምንም ጎጅነት እንደሌለው አረጋግጧል፡፡

የጨረሩ ምግቦች ራዱራ(Radura) የሚባል ምልክት ያስቀምጣሉ፡፡

ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ምግብን የማጨረር ቴክኖሎጅ ማይክሮ ኦርጋኒዝሞችን፣ ባክቴሪያዎችን፣ ፓራሳይቶችን ምግብ ወለድ በሽታዎችን በመግደል የምግብን እድሜ ያራዝማል፡፡

አንዳንዶች ተሟጓቾች ምግብን ማጨረር ምግብን ለጨረራ ማጋለጥ ለካንሰር የሚያጋልጥና የምግብን ቫይታሚን የሚቀንስ ነው ቢሉም አለም አቀፉ የጤና ድርጀት ከ500 በላይ ጥናቶችን በማድግ ሙግቱን ውድቅ ያደርገዋል፡፡

ዛሬ ባለማችን ምግብን ማጨረር ቴክኖሎጅ ከ 40 በላይ በሚሆኑ የምግብ አይነቶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ከ 40 በላይ ሀገራት ጠቀሜታውን አረጋግጠው በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡

ሀገራችንም በዚህ ቴክኖሎጅ በመጠቀም በመጋዘን የተከማቹ ሰብሎች እንዳይበላሹ፣ ምግብ ወለድ በሽታዎችን በማስወገድ የህብረተሰቡን ጤና በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምግቦችን አለም አቀፍ ተፈላጊነት ለማረጋገጥ፣ አለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር፣ የግብርና ምርት ብክነትን ለመቀነስ ቢያንስ አንድ የምግብ ማጨረር ቴክኖሎጅ ተግባራዊ ማድግ ይገባል፡፡

www.iaea.org/worldatom/inforesource/other/food/
www.fda.gov
www.food-irradiation.com


የጨረራ ቪድዮ

የኢ.ጨ.መ.ባ 2005 ዶክመንተር ቪድዮ.


Your Feed back

Detail address

 

 

መነሻ ገጽ | ስለ እኛ | አገልግሎታችን | ጨረራ | አድራሻችን | ወደ ላይ
© ኢ.ጨ.መ.ባ , 2006