የኢ.ጨ.መ.ባ አዳዲስ ዜናዎች

የጨረራ መከላከያ ህግ ሳያከብሩ ሲሰሩ የተገኙ ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች የራጅ ክፍሎች እንዲታሸጉ ተደረገ፡፡ በ2008 በጀት አመት በመጀመሪያ ሩብ አመት የባለስልጣኑ የጨረራ መከላከያ መኮንኖች በአዲስ አበባ፣ ቡታጅራ፣ ሀዋሳና ሻሸመኔ በሚገኙ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች የጨረራ ህክምና ክፍሎች ላይ ባደረጉት ፍተሻ በሰውና አካባቢ ላይ የጨረራ ብክለት መኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎች ጥራት ማነስ፣ ያለፈቃድ መስራትና በወቅቱ ፈቃድ አለማሳደስ በህክምና ተቋማት ዘንድ በክፍተትነት የተለዩ ችግሮች ሆነዋል፡፡በዚሁ የቁጥጥር ሂደት ወቅት 7 የህክምና ተቋማት የራጅ አገልግሎት ክፍሎች እንዲታሸጉ የተደረገ ሲሆን ጉዳያቸው በህግ እንደሚታይም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡፡

የጨረራ አመንጭ ቁሶችና መሳሪያዎች በአለማችን ብሎም በሀገራችን በግብርናው መስክ በእንዱስትሪው በህክምናው እና በጥናትና ምርምር ዘርፍ በርካታ ጥቅም እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም የጨረራ ቁሶችና መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ በአግባቡ ስራ ላይ ካልዋሉ በሰውና በአካባቢ ብሎም በመጭው ትውልድ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣንም በተሻሻለው አዋጅ 571/2000 የጨረራ አመንጭ ቁሶችና መሳሪያዎች አጠቃቀምን ይቆጣጠራል፡፡

በአዋጁ እንደተገለጸው ማንኛውም ያለባለስልጣኑ ፈቃድ የኒውክለር ቁስን የሚይዝ ግለሰብ ወይም ተቋም ከ1 አመት እስከ 3 አመት በሚደርስ እስራት ወይም ከብር 10,000 እስከ 50,000 በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ወይም በሁለቱም እንሚቀጣ በአዋጁ ክፍል አራት አንቀጽ 28 መደንገጉንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ማንኛውም ተቋም የጨረራ አመንጭ ቁሶችና መሳሪያዎችን ያለፈቃድ መጠቀም ማዘዋወር ማዋስ እና ከመሳሰሉት ተግባራት እንዲታቀብና የባለስልጣኑን የቁጥጥር መስፈርት አሟልቶ በህጋዊ መንገድ ብቻ ስራ ላይ እንዲያውል የሚመከር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን በጨረራ ደህንነትና ጥበቃ ዙሪያ ከሁሉም ክልሎች ከመንግስት ሆስፒታሎች ለተወጣጡ ራዲዮግራፈሮችና ራድዮሎጅክ ቴክኖሎጅስቶች በአዲስ አበባ ሰሜን ሆቴል ከግንቦት 10-12 ቀን 2007ዓ.ም የግንዛቤ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የስልጠናው አላማ በህክምናው ዘርፍ በመንግስት ሆስፒታሎች በጨረራ አመንጭ መሳሪያዎች ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች የሆኑት ራድዮግራፈሮችና ራዲዮሎጅክ ቴክኖሎጅስቶች ስለጨረራ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ከተጓዳኝ ጉዳቱ እንዲጠበቁ በሚያደርጉት ጥንቃቄ ለማገዝ ነው፡፡

ፕሮግራሙን በመክፈቻ ንግግራቸው የከፈተቱት አቶ አወቀ ሽፈራው እንደገለጹት ራዲዮግራፈሮችና ራድዮሎጅክ ቴክኖሎጅስቶች እራሳቸውንና ህመምተኞችን ካላስፈላጊ ጨረራ መጠበቅና የጨረራን መሳሪያ በአግባቡና በመስፈርቱ መሰረት በጥንቃቄ ስራ ላይ እንዲያውሉት ባለስልጣኑ በየጊዜው የግንዛቤና የመረጃ ልውውጥ መድረኮችን በማዘጋጀት ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መድረኩን ተጠቅመው የራድዮግራፈርና የራዲዮሎጅክ ቴክኖሎጅስቶች ማህበር ስለማህበራቸው አላማና ተግባር ያብራሩ ሲሆን ባለስልጣኑ የሚያደርግላቸውን ድጋፍ በማህበራቸው ስም አድንቀዋል፡፡

በዚህ የግንዛቤ መድረክ ስለጨረራ ምንነት፣ ፋይዳ፣የጨረራ መለኪያ መሳሪያ፣ስለራጅና አሰራሩ፣ስለጨረራ አደጋና የመከላከያ መንገዶችና ሌሎችም ርእሶች በሰፊው በባለስልጣኑ ባለሙያዎች ይቀርባሉ፡፡

የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሰልጣን ከአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ለተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በጨረራ ፅንሴ ሀሳብ ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ በአማራ ብዙሃን የመሰብሰቢያ መገናኛ አዳራሽ ከሚያዝያ 24-25/2007 ዓ.ም. በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ ቁጥራቸው 41 የሚጠጉ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሰትፏል፡፡

በስልጠናው መክፍቻ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ የማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዋና የስራ ሂደት የመረጃና ጥንቅር የቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታደለ ነጋሽ ባደረጉት ንግግር የስልጠናው ዓላማ የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም በጨረራና ኒኩሌር ቴክኖሎጂ ዙረያ በመረጃና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ ኖሯቸው ጨረራ የሕብረተሰቡ የዕለት ከዕለት አጀንዳ እንዲሆን በማድረግ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ ያለመ እንደሆን ገለፀዋል፡፡ አቶ ታደለ አያይዘው እንደተናገሩት የጨረራንና የኒኩሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ልማት በስፋት እየተጠቀሙ ጨረራ በአካባቢ በንብረት በአሁኑና በመጪው ትውልድ ላይ የሚፈጥራቸውን ተጓዳኝ ጉዳቶች ለሕብረተሰቡ በማስገንዘብ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡

ሁለት ቀን በፈጀው የሰልጠና መድረክ ላይ ሰለጨረራ የሚያውሱ ልዩ ልዩ ጽሐፎች በባለስልጣኑ ባለሙያዎች የቀረቡ ሲሆን በተለይም የጨረራ ዋና ዋና ፋይዳዎችና ጠንቆቻቸው የጨረራ ስነ ሕይወታዊ ጉዳቶችና የመከላከያ ዘዴዎችን እንዲሁም የራዲዮሎጂካል ገጠመኞች እና አደጋዎች የሚሉ የስልጠና ርዕሶች ይገኙበታል፡፡ ጨረራን ከመከላከል አንፃር የልማታዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ሚና ምን መምስል እንደለበት ጽሑፋዊ ገለፃ ተደርጓል፡፡

በቀረቡት የተለያዩ ገለፆዎች ከተሳታፊዊች ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎቹ ከባለሙያዎቹ በቂ ምላሽና ትንታኔዎች ተሰጥቷል፡፡በመጨረሻም በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደተገለፀው በጨረራ ሕብረተሰቡና አካባቢ እንዳይጉዳ ጋዜጠኞች በሚቀርፁቸው መርሃ ግብሮች ጨረራ የሕብረተሰቡ የዕለት ከዕለት አጀንዳ እንዲሆንና የሚፈለገው የአሰተሳሰብ ለውጥ እንዳመጣ ተግተው እንዲሰሩ የባለስልጣኑ የመረጃና ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አራጌ ክብረት መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የሰልጠናው መርሃ ግብር በስኬት ተጠናቋል፡፡

የባለስልጣኑ የማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዋና የስራ ሂደት ከየካቲት 11 – 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በኤም ኤን ኢንተርናሽናል ሆቴል ባማዘጋጀው ስልጠና ላይ ቁጥራቸው ከ33 ለሚሆን የጨረራ ቁስ ተጠቃሚ ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን ባለሙያዎቹ የመጡት ከመጠጥ አምራች ፍብሪካዎች ሲሆን በዋነኛነትም የሌቪል ጌጅ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ባለሙያዎቹ የመጡት ከመጠጥ አምራች ፍብሪካዎች ሲሆን በዋነኛነትም የሌቪል ጌጅ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ጊ/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ብርሃነ መስቀል ቁምቢ ባስተላለፋት መልዕክት ስልጠናው በአይነቱ ልዩ እንደሆነና በተለይም ለሌቪል ጌጅ ተጠቃሚዎች መስጠቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ድርሻው የላቀ መሆኑን ገልፀው አገራችን ኢትዩåያ ከምን ጊዜውም በተሻለ ሁኔታ የጨረራ ቴክኖሎጂ በስፋት ለልማት ተግባራት እየተጠቀመች መሆኑንና በመስኩ የሚደረገው የጥናትና ምርምር ስርዓት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአብራሩ በኃላ የጨረራን ቴክኖሎጂን ለልማት ስንጠቀም ጨረራ በአካባቢ ፣በንብረት ፣በጤናና እንዲሁም በአሁኑና በመጪው ትውልድ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅኖ ለመከላከል የሚደረገውን የቁጥጥር ስርዓት ለማጠናከር ስልጠናው ዘርፍ ብዙ ፋይዳዎች እንደሚኖሩት በአፅኖት ተናግረዋል፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ የባለስልጣኑ የመረጃና ህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ጊዜያዊ ተወካዬ አቶ ሽመልስ ሱፋ በአቀረቡት ፅሁፍ ባለስልጣኑ እያከናወናቸው የሚገኙት እንቅስቃሴዎችና ተግባራት በዝርዝር ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በተለይም በሁለቱ ዋና የስራ ሂደቶች የተገኙ ተጨባጭ የለውጥ ውጤቶችን ለተሳታፊዎች በዝርዝር ከአብራሩ በኋላ ባለስልጣኑ የሚያደርጋቸውን ቅንጅታዊ አሰራሮች የበለጠ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡ ሁለት ቀን በፊጀው የስልጠና መርሀ ግብር በጨረራ ቁጥጥርና ድህንነት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ልዩ ልዩ ፅሁፎች የቀርቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል

 • የጨረራ ምንነትና አይነቶቻቸው
 • የNDG እና NDT አይነቶችን ፋይዳዎቻቸው የጨረራ ቁስ አሀዶች / unit/ የጨረራ ራዲዬሎጂካል ቅደም ጥንቃቄዎችና ምላሾች ና ሌሎችም ሰፊና ጥልቅ ርዕሰ ጉዳዬች በበቂ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች በመደገፍ ለተሳታፊዎቹ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
 • በዚህም መሰረት በርዕሱ ለተዳሰሱ አበይት ጐዳዬች ከተሳታፊዎች ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ቀርበው የባለስልጣኑ ባለሙያዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡በመጨረሻም የባለስልጣኑ የማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ የመረጃና ጥንቅር ቡድን መሪ አቶ ታደለ ነጋሽ በስልጠና ማጠቃለያው ላይ ከተሳታፊዎች በቲ ኤ ሊዲ ንባብ በተቋሞቻቸው በሚያጋጥሙ ወቅታዊ ችግሮች በባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የዕለቱ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡

  ከየካቲት 2-6ቀን2007ዓ.ም በአለምአቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ ትብብር ለ15 የባለስልጣኑ የጨረራ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች በማሞግራፊና በሲቲስካን የጨረራ ህክምና መሳሪያዎች ላይ የንድፈሃሳብና የተግባር ስልጠና በዶር.ናዳ አባስ ተሰጠ፡፡የስልጠናው አለማ በሲቲና ማሞግራፊ ላይ ያለን ክፍተት በመሙላት የተሟላ የጨረራ ቁጥጥር ለማድረግ ነው፡፡፡

  ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የባለስልጣኑ ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሀነመስቀል እንደገለጸቱት አለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ አባል ሀገራትን በጨረራና ኒውክለር ቁጥጥር ዘርፍ የሚሰጠውን የስልጠና ድጋፍ አድንቀው በሀገራችን ላይ ከምንግዜውም በላይ እንዚህ የህክምና የጨረራ መሳሪያዎች በመስፋፋት ላይ መሆናቸው ተገቢው ቁጥጥር ለማድረግ ይህ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ነው፡፡

  ስልጠናው አዲስ አበባ በሚገኙ ሲቲ ስካንና ማሞግራፊ መሳሪዎች ባሉበት በቤተዛታ ሆስፒታል፣በውዳሴ የህክምና ማእከል፣በሲኖሞካሺ ሆስፒታል፣በኮሪያ ሆስፒታልና በሌሎችም ስፍራዎች የህክምና ተቋማት ተግባራዊ የኢንስፔክሽን ስራዎች ኢንስፔክሽን መስራት እንደሚቻል በዶር. ናዳ አባስ በመታገዝ ተግባራዊ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የሱዳን ጨረራ ሰራተኛ የሆኑት ዶክተሯ ሰልጣኞች እውቀቱን ለመቅሰም ያላቸውን ተነሳሽነት ማድነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

  ባለሰልጣኑ በካሌብ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጥር 05 ቀን 2007 ዓ.ም ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀሙን ለባለድርሻ አካላት አቅርቦ በስፋት ያስገመገመ ሲሆን በሪፖርቱ ዋና ዳሬክተሩን በመወከል ያቀረቡት አቶ ዋሲሁን አለማየው ጊዚያዊ የዳሬክተሩ አማካሪ በሪፖርቱ ለመጠቆም እንደሞከሩት ባለስልጣኑ እየከናወነ ያለውን ዋና ዋና ተግባራት በተለይም በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያሉትን ጥንካራ የሬጉላቶሪና የኢንስፔክሽን ስራዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልፀው ፡፡በተለይም መስፈርቱን አሟልተው በማይሰሩ የመንግስትና የግል የጤና ተቋማት ላይ ከሌላው የበጀት ዓመት በተለየ በያዝነው የበጀት ዓመት ጥንካራ የቁጥጥር ስራዊች እንደተሰሩና አስፈላጊውን መስፈርት በማያሟሉት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዳል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በሪፖርቱ ላይ እንደተገለፀው የለውጥ ሰራዊት ግንባታው የተጠበቀውን ያክል ውጤታማ ባይሆንም ጀምሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

  አቶ ዋስሁን አለማየው አክለው እንደገለፁት ባለስልጣኑ በሰው ሀይል ልማት ስልጠናዎች ጠንካራ ተግባራትን እያከናወኑ እንዳለና በቀጣይም ጊዜያት የተሻለ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በደላቀ ደረጃ ለማሽጋገር ጥረቶች እየተደረጉ እንዳለ ተናገረዋል፡፡ሌላው በሪፖርታቸው ለመጠቆም እንደሞከሩት ባለሰልጣኑ የሰው ሀይል ፋልሰት የግባአት አቅርቦት ና ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ ከመስራት አንፃር እንደጥረት የሚነሱ ጉዳዬች ናቸው ፡፡በዕቅድ ግምገማው ላይ የባለስልጣኑ የህዝብ ክንፍ ማህበራት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አቅርበው የልምድ ልውውጥ የተደረገባቸው ሲሆን የዚህ አይነቱ ተሞክሮ በቀጣይ መድረኮች የበለጠ እንዲዳብሩ የጋራ ስምምነት ተይዟል፡፡በመጨረሻም በሪፖርቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበት የዕለት መርሀ ግብር ተጠናቋል፡፡

  የባለሰልጣኑ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ዋና የስራ ሂደት ለውሃ አምራቾች ለምግብ አስመጪዎች አስገዳጃ በሆኑ የጨረራ ደረጃ ላይ በአምባሳደር ሆቴል ታህሳስ 14 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት ባለድርሻ አካላት እንደገለፁት የዚህ አይነት የምክከር መድረክ መዘጋጀቱ የህብረተሰቡን ጤንነት ለመጠበቅና አካባቢን ከጨረራ አደጋ ለመከላከል የላቀ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር ባቀረቡት ገለፃ አስገዳጃ የጨረራ ደረጃዎችን በቀጥታ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት መሰጠቱ በቅንጅት ለመስራት ዕድል እንደሚፈጥር አብራርቷል፡፡በተጨማሪም እነዚህ የውሃ አምራቾችና የምግብ አስመጪዎች በሚያውላቸው የፍጆታ ዕቃዎች ላይ አስፈላጊውን የጨረራ ይዘት መጠን ተገንዝበው የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታትና ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ ለማሳለጥ የመድረኩ ጠቀሜታ ሰፊ እንደሆነ አብራርተው ፡፡ባለሰልጣኑ በቀጣይ ጊዜም የተለያዩ የግንዛቤ መድረኮችን ከነዚህ አካላት ጋር በመፍጠር በአሁኑና በመጪው ትውልድ ላይ ጨረራ ሊፈጥር የሚችለውን ጠንቅ ለመከላከል እንደሚጥር ገልፀዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያያዞ አቶ እሸቱ ጥላሁን የአካባቢና የምግብ ጨረራ ደህንነት ከፍተኛ መኮንን ባቀረቡት ፅሁፍ ውሃዎችና ምግቦች በጨረራ ሊበከሉ እንደሚችሉ ገልፀው በጨረራ ብክለት ዙሪያ ወይም /Radiation Contamination/ ሰፊ ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ባለሙያው አክለው እንደገለፁት ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ የውሃ አምራቾችና ምግብ አስመጪዎች አስፈላጊውን ምዝገባ በመፈፀም ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አብራርተዋል፡፡በቀረቡት ፅሁፎች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በቂ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ ኘሮግራም ተጠናቋል፡፡

  ዘንድሮ አንድም ሰው ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዳይያዝ እንዳይሞትና እንዳይገደል በሚል መሪ ቃል የኤች አይ ቪ ኤድስ ለ26ኛ ጊዜ፣ ከሚከበረው የጸረ ጾታ ጥቃት ያለእድሜ ጋብቻና በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የሀይል ጥቃቶችን በማስቆም ህዳሴያችንን እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃል ለ9ኛ ጊዜ የጾታ ጥቃት ቀን በደመቀ ሁኔታ ህዳር 26 ቀን 2007ዓ.ም በባስልጣኑ ተከብሯል፡፡

  ወረርሽኙ ያስከተለውንና እያስከተለ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ልብ ማለት ይገባል በማለት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በበአሉ መክፈቻ ንግግራቸው የገለጹ ሲሆን አያይዘውም ወረርሽኙ በአለም ሆነ በሀገራችን የአያሌ አምራች ሀይል ህይወት መቅጠፉ ለልማት የምናውለውን ሀይል መሻማቱን ገልጸዋል፡፡

  በእለቱ በጾታዊ ጥቃት ደርሶባት በቅርቡ ሕይወትዋ ያለፈውን ሃናን በማሰብ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎትና የመታሰቢያ ሻማ የማብራት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ተያያጽሁፎችም በተጋባዥ እንግዶች ቀርበዋል፡፡

  በጾታዊ ጥቃት አስመልክቶ ከሴቶችና ወጣቶች ዴስክ የተጋበዙት ጽሁፍ አቅራቢ እንደገለጹት በፌደራል ሲቪል ሰርቪስ የሰራተኞች አዋጅ ላይ ጾታዊ ጥቃት ከፍተኛ ጥፋት ሆኖ መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡በአለም ከ3 ሴቶች መካከል ሴት በህይወት ዘመኗ የወሲባዊ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ይገጥማል፤በአለም ከ7ጥንዶች አንዷ በባሏ ትደፈራለች፤በአለም ከአስግድዶ መድፈር ውስጥ 25ፐርሰንት በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸም ነው፤በቀን 6000ሴት ህጻናት በጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ምክንያት ይገረዛሉ የሚሉ መረጃዎች ለተሳታፊ ቀርቧል፡፡

  የትግራይ የሳይንስ ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ አባላት በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን የልምድ ልውውጥ ትምህርታዊ ጉብኝት 23/03/2007ዓ.ም ያካሄዱ ሲሆን አላማውም ከጨረራና ተያያዥ ተግባራት ተቋማዊ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ነው፡፡

  ዶክተር መኮንን ሀይለስላሴ፣የኤጀንሲው ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር እንደገለጹት ከባለስልጣኑ ጋር የማቴሪያል፣የቴክኒካልና በጋራ ተቀናጅቶ በመስራት ህብረተሰቡን ከጨረራ ጠንቅ ከመጠበቅ አንጻር ውጤታማ ለመሆን ቅንጅታዊ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸውንና ክልሉ ከባለስልጣኑ ሰፊ ትምህርት ያገኘበት ጉብኝት መሆኑን አስረድተው ለተባበሩዋቸው ሁሉ ምስጋናን አቅርበዋል፡፡

  በቅድሚያ ባለስልጣኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት በዝርዝር ለጎብኝዎቹ የቀረቡ ሲሆን በቀጣይ አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው የራዲዮአክቲቭ ዝቃጭ ማከማቻ ማእከል ጉብኝት ተካሂዶ ፕሮገራሙ ተጠናቋል፡፡

  የባለስልጣኑ ማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዳሬክቶሬት ለማእን ልማድት አክስዮን ማህበር አስፈጸሚ አካላት ከ12-13ህዳር 2007ዓ.ም በካሌብ ሆቴል በጨረር ምንነትና ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና ሰጡ፡፡የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶር. ዘሪሁን ደስታ እንደገለጹት ማእድን የሀገራችን አንዱ የኢኮኖሚ መሰረት መሆኑንና አመራረቱም የዘመኑን ሳይናሳዊ መንገድ ተከትሎ እንዲሆን ለማድረግ ከጨረር አመንጭ ማእድናት አንጻር መድረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ለማወቅና ለመተግበር ስልጠናው ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  በስልጠናው ወቅት የባለስልጣኑ የልማት እንቅስቃሴዎች የተገለጸ ሲሀን በተጨማሪ ዋና ዋና አላማዎቹ የጨረራ አመንጪ ቁስ/መሣሪያን ከማግኘት፣ ከማምረት፣ ከመጠቀም ፣ ከማጓጓዝ ፣ ከማስወገድ ፣ ወዘተ ጋር የተዛመዱ ማናቸውንም ተግባራት መወሰን፣ መቆጣጠርና መከታተል እና በጨረራ መከላከያ የምርምርና ሥርፀት ሥራዎችን የማከናወን፣ የማበረታታትና እንዲዳብሩ ማድረግ መሆኑ ታይቷል፡፡ከዚህ አንጻር ታንታለም ማእድን ፍለጋና ለማት ስራ የቁጥጥር መስፈርት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን ይህም በማእድን ቁፋሮ፣በነዳጅ ፍለጋ፣እና በመሳሰሉት የገጸ ምድር ቁፋሮ ወቅት በተፈጥሮ የሚገኙ የጨረራ አመንጭዎች ጨረራ የማውጣት አቅማቸው የሚጨምር በመሆኑ በአካባቢ ህብረተሰብ ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ እንዲቻል የታንታለም ማእድን ፍለጋና ልማት የቁጥጥር መስፈርት ተዘጋጅቶ ለሰልጣኞቹ ተብራትቷል፡፡

  ለጨረራ መጋለጥ የሰው ልጆችን ሴል በመጉዳት እንደጉታቱ አይነትና እንደጨረራው አይነት ለመካንነት፣ለካንሰር፣ለነርቭ መጎዳትና ሞት ማስከተል የሚችል መሆኑ የተብራራ ሲሆን ከጨረራ ጉዳት ለመጠበቅ ግንዛቤ፣ጥንቃቄ እና ሶስቱን መርሆች ማለትም ከጨረራ አካባቢ መራቅ፣ቆይታ መሳጠርና መከላከያ ልብሶች ወይም መሳሪያዎች መጠቀም ተገቢ መሆኑን ተብራርቷል፡፡፡

  በስብሰባ ማዕከል ከጥቅምት 14 እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ባካሄደው ስልጠና ላይ ከ 86ዐ በላይ የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት የአቅም ግንባታ ስልጠና የመንግስት ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች በስፉትና በጥልቀት የተዳሰሱ ሲሆን በስልጠናው ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚንስትር ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ ባስተላለፋት መልዕክት እንደገለፁት የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ የመንግስትን ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች፣ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ተረድቶ ልማታዊ ሲቪል ሰርቪስን በተቋማት ስር እንዲሰድና የአገራችንን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ በ2ዐ17 አገሯችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍና ህዝቡን የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ማድረግ ይቻል ዘንድ የጋራ አቋም ለመያዝ ያለመ መሆኑን ገልፅው፡፡በስልጠናው ሰፊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማስረፅ ዘመናዊ ፣ፈጣን ፣ልማታዊ፣ ቀልጣፋ፣ ስቪል ሰርቪስን መገንባት ነው፡፡

  በስልጠናው ላይ አምስት መሰረታዊ የመንግስት የፖሊሲና፣የስትራቴጂ ሰነዶች ቀርበው በቂ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከመድረክ መሪዎችና ከተሳታፊዎች በቂ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡በተለይም ከብዛሃነት ከዲሞክራሲ ግንባታና ከህግ መንግስት ፣ከሰኩላሪዝም አንፃር ለተነሱ ጥያቄዎች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መያዝ ተችሏል፡፡

  በስልጠናው ላይ አዝናኝና አስደሳች የስነ ፅሁፍ ውጤቶችን በማቅረብ ተሳታፊዎች አመራሮ እንዲዝናኑ ተደርገዋል፡፡

  በስልጠናው ማጠቃላያ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚንስትር ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ ባስተላለፋት መልዕክት አገራችን ኢትዮåያ የብዙ ብሔርብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር በመሆኗ ብዛሃነትን አጠናክሮ መቀጠል ለነገ የማይባል የቤት ስራ እንዳልሆነ ተረድቶ ዲሞክራሲያዊ አመለካከትን በመከተል አገራችን ለተያያዘችው የህዳሴ ጉዞ የበኩላችንን አስተዎፆ ማድረግ ከእያንዳንዱ ስቪል ሰርቫንት ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም በየተቋማቱ በሲቪል ሰርቪሱ የሚታዩ የአመለካከት ፣የግባአት፣የክህሎት ክፍተቶችን በመድፈን የተጣለብንን አገራዊ ኃላፊነት መወጣት አለብን በማለት አሳስበዋል፡፡በመጨረሻም በስልጠና ላይ የተሳተፋ መካከለኛ አመራሮችና ፈጻሚ ሰራተኞች ባለ 1ዐ ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ በማውጣትና ለተግባራዊነቱ ቃል በመግባት ስልጠናው ያለምንም እንከን ተጠናቋል፡፡

  በአገር አቀፍ ደረጃ ለ 8 ጊዜ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማስመልከት የባለሰልጣኑ ሰራተኞች በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥቅምት 3 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. ባከበሩበት ወቅት የተገኙት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር ባስተላለፋት መልዕክት በየአመቱ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ማክበር ለአገራችን ብሔረብሄረሰቦች እና ህዝቦች የላቀ ፋይዳ ትርጉም እንዳለው ከገለፁ በኋላ አገራችን እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር የሲቪል ስርቪስ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የህዳሴ ጉዞችንን የበለጠ ለማፋጠን በየጊዜው የተቋማችንን አሰራር ግለፀኝነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ ደንበኞ ተኮር አገልግሎትን ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

  የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ አራጌ ክብረት በሽብር አዋጅ ዙሪያ መግለጫና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮåያ ህዝብ መዝሙር ተዘምሯ የበዕሉ ፈጻሜ ሆኗል፡፡

  ባለስልጣኑ መስከረም 6 ና 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በሽራተን አዲስ በተካሄደው አወደ ጥናት ላይ ተሳታፊ ሲሆን የአወደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በኒውክለር ጥበቃ ደህንነትና ፀጥታ ፖሮቶኮል ዙሪያ ያለውን ተሞክሮ ለመቅሰም ያለመ ነው፡፡በአውደ ጥናቱ ላይ ቪርቲክ የተባለው ድርጅት የኒውክለር ጠበቃ ደህንነት እገዳን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችን በባለሙያዎች ያቀረበ ሲሆን በአወደ ጥናቱ ላይ ከፍዴራል መንግስት የተወጣጡ 9 ተወካዩች ተገኝቷል ፡፡ ከነዚህም መካከል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣የፍትህ ሚኒስተር፣ የከፍተኛ ተቋም ፣ የህግ ትምህርትቤችና ተወካዬች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር በመክፍቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ይህ አይነቱ አለም አቀፍ አወደ ጥናት አገራችን ኢትዩጵያ የኒውክለር ደህንነት ጥበቃና እገዳ ፖሮቶኮል ከመፈረሟ በፊት ያሉትን ቅደመ ሁኔታዎች ለማጥናትና ያለውን ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ በጥልቀት መገምገም አስፈላጊ እንደሆነ ተናግራዋል፡፡

  አወደ ጥናቱ በሁለት ቀን ቆይታው የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ከቤቱ አስተያየቶና ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የኒውክሌር ጥበቃ ደህነት እገዳ ፖሮቶኮል 147 አገሮች የፈረሙ ሲሆን 124 ደግሞ ፊርማውን በማፀደቅ በስራ ላይ እንዲውል አድርገዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የየሀገሩ ተሞክሮዎች ቀርበዋል፡፡በተለይም የካናዳ የደብብ ኮሪያ፣ዩናይትድ አረብ ፣በማሳያነት እንድ አብነት ተጠቃሾት ናቸው፡፡ በአወደ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የባለስልጣኑ የስራ እንቅስቃሴ በፅሁፍ አብራርተዋል፡፡ መጨረሻም የዚህ አይነቱ አወደ ጥናቱ በቀጣይ ጊዜያት የጋራ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልፆ በስኬት ተጠናቋል፡፡

  ባለስልጣኑ መስከረም 6 ና 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በሽራተን አዲስ በተካሄደው አወደ ጥናት ላይ ተሳታፊ ሲሆን የአወደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ አገራችን ኢትዮጵያ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በኒውክለር ጥበቃ ደህንነትና ፀጥታ ፖሮቶኮል ዙሪያ ያለውን ተሞክሮ ለመቅሰም ያለመ ነው፡፡በአውደ ጥናቱ ላይ ቪርቲክ የተባለው ድርጅት የኒውክለር ጠበቃ ደህንነት እገዳን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችን በባለሙያዎች ያቀረበ ሲሆን በአወደ ጥናቱ ላይ ከፍዴራል መንግስት የተወጣጡ 9 ተወካዩች ተገኝቷል ፡፡ ከነዚህም መካከል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣የፍትህ ሚኒስተር፣ የከፍተኛ ተቋም ፣ የህግ ትምህርትቤችና ተወካዬች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር በመክፍቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ይህ አይነቱ አለም አቀፍ አወደ ጥናት አገራችን ኢትዩጵያ የኒውክለር ደህንነት ጥበቃና እገዳ ፖሮቶኮል ከመፈረሟ በፊት ያሉትን ቅደመ ሁኔታዎች ለማጥናትና ያለውን ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ በጥልቀት መገምገም አስፈላጊ እንደሆነ ተናግራዋል፡፡

  አወደ ጥናቱ በሁለት ቀን ቆይታው የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ከቤቱ አስተያየቶና ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የኒውክሌር ጥበቃ ደህነት እገዳ ፖሮቶኮል 147 አገሮች የፈረሙ ሲሆን 124 ደግሞ ፊርማውን በማፀደቅ በስራ ላይ እንዲውል አድርገዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የየሀገሩ ተሞክሮዎች ቀርበዋል፡፡በተለይም የካናዳ የደብብ ኮሪያ፣ዩናይትድ አረብ ፣በማሳያነት እንድ አብነት ተጠቃሾት ናቸው፡፡ በአወደ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የባለስልጣኑ የስራ እንቅስቃሴ በፅሁፍ አብራርተዋል፡፡ መጨረሻም የዚህ አይነቱ አወደ ጥናቱ በቀጣይ ጊዜያት የጋራ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልፆ በስኬት ተጠናቋል፡፡

  ባለስልጣኑ ያስገነባውን ዘመናዊ ማዕከል ጳጉሜ 01 ቀን 2006 በ.ኢ.ፌ.ድ.ረ.ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚኒስትር ወ/ሮ ደማቱ ሀምቢሳ ና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተመረቀ፡፡

  በምረቃ ሰነ ሰርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክብርት ሚ/ሯ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት የማዕከሉ በይፋ ተመርቆ ሰራ መጀመረ ለሀገራችን የሚኖረው ፋይዳ እጅግ በርካታ እንደሆነ ገልፀው በምሰራቅ አፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነው ማዕከል ለ5ዐ ዓመታት አገልግሎት እንደሚሰጥ ታምኖበታል፡፡

  የራዲዮአክቲቭ ዝቃጭ ቁሶችን በአንድ ማዕከላዊ ቦታ ማቀናበርና ማከማቸት በጨረር ዙሪያ የሚደረገውን የመከላከልና ተጋላጭነት ለመቀነስ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡ በቀጣይ ጊዜያትም ሌሎት ተጨማሪ ማዕከላት ለማስገንባት መንግስት ጥረት እንደሚያደርግ ግልፀዋል፡፡ እንደዚሁም የሚኒስትር መሰሪያ ቤታቸው ለባለስልጣኑ የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባስተላለፉት መልዕክት አረጋግጠዋል፡፡

  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ማዕከሉን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 5 ዓመት እንደወሰደና ለግንባታውም ማስፈፀሚያ ከ1ዐ ሚሊየን ብር በላይ ፈሰሰ እንደተደረገ ገልፀው የግንባታው ወጩ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡

  አያይዘውም የማዕከሉ ግንባታ ለሀገራችን የሚኖረው ፋይዳ የላቀ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

  በተለይም ማዕከሉ የልቀት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግልና ባለቤት አልባ የራዲዮ አክቲቭ ቁሶችን በተከታታይ ለመቆጣጠር ዕድል ይፈጥራል በማለት ተናግረዋል፡፡

  በመጨረሻም በምረቃ ስነሰርዓቱ ላይ በግንባታው ሂደት አስተዋፅኦ ላደረጉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች የዕውቅናና የምስክር ወረቀት በክብርት ሚኒስትሯና በዋና ዳይሬክተሩ ተበርክቶላቸው የዕለቱ የምረቃ ሰነስርዓት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

  የጨረራና ኒውክለር ቴክኖሎጅ በሀገራችን በልዩ ልዩ የህክምናና የኢንዳስትሪ ዘርፎች በመስፋፋት ላይ ሲሆን በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ከቁጥጥር በተጓዳኝ ለጨረራ ሰራተኞች የግንዛቤ ስልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባስተከላቸው የካርጎ ስካኒንግ ማሽን ላይ ለሚሰሩ 62 ለሚሆኑ የጨረራ ሰራተኞች በባለስልጣኑ ማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት የጨረራ መከላከልና ደህንነት የግንዛቤ ስልጠና ከነሀሴ23-29ቀን2006ዓ.ም በሚሌና በጋላፊ ተሰጠ፡፡

  በስልጠናው ወቅት የተገኙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የስራ አካባቢ የጤና ባለሙያ አቶ አህመድ መሀመድ ባለስልጣኑ ይህን ሁሉ መንገድ ተጉዞ ለጨረራ ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና በመስሪያ ቤታቸው ስም አመስግነው ሰልጣኞች በሚገባ ሰአት አክበረው እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡

  ሰልጣኞች ስለጨረራ ምንነነትና አፈጣጠር፣ስለጨረራ መጠን መለኪያ መሳሪያዎች ንባብና አጠቃቀማቸው፣ስለድንገተኛ የጨረራ አደጋዎችና ክስተቶች፣ስለድንገተኛ ዝግጁነት እቅድ፣ስለጨረራ መሳሪያዎችና ቁሶች ከለላና ጥበቃ፣ስለካርጎ ስካኒንግ መስፈርቶች፣እና ስለከጨረራ እራስን የመከላከያ መርሆች በሰፊው ስልጠና ወስደዋል፡፡

  በስልጠናው መጨረሻ ቀን በነበረው ውይይት ሰልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችንና ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ይኸውም አብዛኞቹ አዲስ ተቀጣሪዎች በመሆናቸውና ስለጨረራ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም በተደረው የቲኤልዲ ንባብ የተወሰኑት ኦቨር ዶዝ የሚል ንባብ መኖር፣ሰርቬይ ሜትር ካለመጠቀማቸውን እንዲሁም ስለጨረራ ህክምናና መሰል ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል፡፡አሰልጣኞቹም ማንኛውም ተቋም የጨረራ መሳሪያ ወይም ቁስ ለመጠቀም ቅድሚያ የባለስልጣኑን ፈቃድ ማግኘት እንዳለበትና በወቅቱም ማደስ እንዳለበት ገልጸው የጨረራና ኒውክለር ቴክኖሎጅ በአግባቡ ስራ ላይ ካዋልነው ምንም ጉዳት ሊያደርስ ስለማይችል ስጋታቸውን ማስወገድ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡በየጊዜውም ሰርቬይ ሜትር በመጠቀም የስራ አካባቢያቸውን ሴፍቲ ኦፊሰሩ መፈተሽ እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡

  ምንም እንኳን ሜሌና ጋላፊ ከፍተኛ ሙቀት፣እንደደመና የሚከብ ከባድ ንፋስ፣ጊንጥና መሰል ተናዳፊ ነፍሳት ያሉበት፣የተመቻቸ የስልጠና ስፍራ የሌለበት ቢሆንም ባለስልጣኑ ሰራተኞች ስለሰጡት ስልጠና ሰልጣኞችና ሀላፊዎቻቸው ምስጋና ችረዋል፡፡፡

  በጋላፊ ከካርጎ ስካኒንግ ማሽን በተጨማሪ አላስፈላጊ የጨረራ ቁሶች፣ በጨረራ የተበከሉ መሳሪያዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡና ከሀገርም እንዳይወጡ ለመፈተሸና ለመለየት የሚረዱ ሲካን የሚባሉ ሁለት መሳሪያዎች ተተክለዋል፡፡

  የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የፊስክስ መምህራን " የጨረራ ደህንነት የግንዛቤ ስልጠና " በሚል ርእስ በካሌብ ሆቴል ከሚያዝያ 21-22 ቀን 2006ዓ.ም የሁለት ቀን ስልጠና የሰጠ ሲሆን አላማው የመምህራኑን ግንዛቤ በጨረር ምንነት ላይ ግንዛቤ ማሳድግ ነው፡፡

  በመክፈቻው ንግግራቸው እንደገለጹት መምህራኑ ከጨረር ጋር በካሪኩለሙ የተገናኙ በመሆኑ በጨረር ምንትና ደህንነት ባህል ግንዛቤያቸውን ማሳደጉ ሰፊ ቁጥር ያለውን ተማሪዎቻቸውንም መድረስ ከመሆኑና ከመስኩ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥ አካላት በመሆናቸው አስፈላጊነቱ አብራተዋል፡፡

  ስልጠናውን ያዘጋጁት ከማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ሲሆኑ በባለስልጣኑ አወቃቀርና አመሰራረት ዙሪያ፣ በጨረር ቁስ ምንነትና ጽንሰ ሃሳብ ፣ በጨረራ መለኪያ ዩኒቶች፣የጨረርና ኒውክለር ጥቅሞች፣የጨረራ መለኪያ መሳሪያዎች፣የጨረራ ስነህዋሳዊ ጉዳቶችና አደጋዎች ፣ከጨረራ ጠንቅ መከላከያ መንገዶች ወዘተ በስልጠናው የተካተቱ ነጥቦች ናቸው፡፡

  ባለስልጣኑ አሁን ላይ በተሻሻለው አዋጅ 571/2000 የጨረርና ኒውክለር ቴክኖሎጅ በልዩ ልዩ መስኮች ለልማት ሲውል በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል የሚቆጣጠር ሲሆን ይህም ህዝብንና አካባቢን ከተጓዳኝ ጉዳት ለመጠበቅ የሚደረግ ተግባር መሆኑ ተብራርቷል፡፡ጨረር በኢንዳስትሪ ፣ በትምህርትና ምርምር ዘርፍ፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ በህይል አማራጭነት ፣ በህክምና ዘርፍ ወዘተ በርካታ ጠቀሜታ እየሰጠ ሲሆን የግንዛቤ ባህል ማዳበር ከጉዳቱ መጠበቂያ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ከጨረር መሳሪያ ወይም ቁስ ባልተፈለገ ሁኔታ ከተጋለጠ እንደጨረሩ አይነትና የቆይታ መጠን ስነህዋሳዊ ጉዳት የሚደርስበት ሲሆን ከበዛም ሊሞት እንደሚችል ተብራርቶ ከጨረር እራስን ለመጠበቅ በአካባቢው የቆይታ ጊዜ ማሳጠር፣መራቅና መከላከያ ልብሶችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን በስልጠናው ወቅት ተብራርቷል፡፡

  በመጨረሻም ሰፊ ውይይት የቀረበ ሲሆን ለሰልጣኞች ሰርተፊኬት ተሰጥቶ የፕሮግራም ማጠናቀቂያ ሆኗል፡፡

  ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካለት ጋር ሚያዘያ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትጵያ ሆቴል በካሄደው የምክክር አውደ ጥናት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር የተቋማቸውን የ9ኛ ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት እየተጠናከር መምጣቱን ገልፀው ይህ ጅምር ግንኙነት ወደ ፊትም ተጠናክሮ እንዲሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

  በሪፖርታቸው በዝርዝር ካቀረቡአቸው ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች መካከል በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና የስኬት ለውጦች ፣የሰው ሀይል ቅጥር፣የአገርውስጥና የውጭ ሀገር የትብብር ስምምነቶች የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተቋማዊ ገጽታ የመልካም አስተዳዳር ግንባታዎች እና በበጀት ዓመቱ የታዮ ተግዳሮቶችን ዳስሰዋል ፡፡በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከህዝብ ክንፍ ለተነሱት ጥያቄዎች ስፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ የማሳወቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሱሩር ከድር የ5ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአፈፃፀም ደረጃ የሚገኝበትን ሁኔታና ያጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ባለድርሻ አካላቱ በስፉት እንዲወዩበት ካቀረቡ በኋላ ለተነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ከቤቱ በቂ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ከዚህ ባሻገር የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሪት ዙልፉ አብዶ የሳይንስ ሙያ ማህበራት ተሞክሮ በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ከአቀረቡ በኋላ ከክፍሉ ባለሙያ የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ምርጥ ተሞክሮዎች ቀርቦ የሀሳብና የልምድ ልውውጥ ሊደርግበት ችሏል፡፡በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ በመዝጊያ ንግግራቸው እንደገለፁት የህዝብ ክንፍዎቹ ለባለስልጣኑ ውጤታማነት ወሳኝ አጋሮች በመሆናቸው የሚደረገው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እንደማይለያቸው አረጋግጠውላቸዋል፡፡

  የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን ቀድሞ ይጠቀምበት የነበረውን የሬጉላቶሪ ባለስልጣን ኢንፎርሜሽን ሥርዓት ( RAIS 3.0) ሶፍትዌር በተሸሻለው የሬጉላቶሪ ኦቶሪቲ ኢንፎርሜሽን ሥርዓት (RAIS-3.2) ሶፍትዌር በመተካት በባለስልጣኑ ተመዝግበው የነበሩ ሀገራዊ የጨረራ አመንጪዎችና ተያያዥ መረጃዎችንም አዲሱን ሶፍትዌር በመጠቀም ከዓለምአቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በድጋፍ ወደተገኘው ሠርቨር ኮምፒዩተር ሙሉ በሙሉ የማሸጋገር ተግባር አከናውኗል፡፡

  ባለስልጣኑ ተግባራዊ ያደረገው አዲሱ ሶፍትዌር የሬጉላቶሪ ስራውን ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚስችለው አጋጣሚን የሚፈጥርለት ሲሆን ኢንስፔክተሮች ከቢሮውጭ ሆነው የኢንስፔክሽን ውጤትን እና ተያያዥ መረጃዎችን የማስገባትና መረጃም የማግኘት አቅም የሚፈጥርላቸው ሲሆን በርቀት ያሉ የባለስልጣኑ የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ከባለስልጣኑ ለነሱ የሚተላለፉ መልዕክቶችም ባሉበት ሆነው በቀጥታ እንዲደርሷቸው እነሱም በቀጥታ ምላሸ መስጠት የሚያስችላቸው ሲሆን በሂደትም አዲስ የአገልግሎት ማማልከቻ ባሉበት ሆነው ማቅረብ የሚያስችል አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ ያስችላል፡፡

  የባለስልጣኑን የመረጃ ሥርዓት ወደዘመናዊነት ለማሸጋገር ተግባራዊ የተደረገውን አዲሱ ሶፍትዌርና ትልቅ አቅም ያለው የሠርቨር ኮምፒዩወተር ከዓለምአቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በድጋፍ የተገኙ ሲሆን አጠቃቀሙን በተመለከተ ለ ባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ባለሙያዎችና ከሁለቱ አላማ አስፈፃሚ ክፍሎች ለተውጣጡ አስር ባለሙያዎች ከMarch 24-28/2014 ድረስ የኤጀንሲው ወደኢትዮጵያ በላካቸው ከፍተኛ ባለሙያ የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

  29 አባላት ያቀፈ (28 ወንድና 1 ሴት ) የመቱ ዩንቨርሲቲ ፊዚክስ ዴፓርትመንት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች መጋቢት በባለስልጣኑ መ/ቤት በመገኘት የግማሽ ቀን ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡

  የትምህርታዊ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ ከጨረራና ኑክሌር ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች በንድፈ-ሃሳብ የቀሰሙትን እውቀት በተጨባጭ ካለውን ጠቀሜታ በመረዳት መነቃቃትን ለመፍጠር ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የገለጹት የፕሮግራሙ አስተባባሪና የዩንቨርሲቲው መምህር የሆኑት አቶ ማስረሻ ትምህርታዊ ጉብኝቱ ተመራቂ ተማሪዎቹ ቴክኖሎጂን የሚፈራ ሳይሆን የሚደፍር ትውልድን በስራ አለምም ችግር ፈቺ ምርምሮችን እንዲያካሂዱ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል፡፡

  በጉብኝቱ መጀመሪያ ለተማሪዎቹ ስለባለስልጣኑ መ/ቤት አመሰራረት ፣ራዕይና ተልእኮ እንዲሁም ስለሚያከናውናቸው ተግባራት በዶክመንታሪ ፊልም የተደገፈ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በስራ ክፍሎች በመገኘት በተለይም በባለስልጣኑ የምግብና አካባቢ ጨረራ ይዘት መጠን ልኬት ቤተ-ሙከራ ሥራ ክፍል ከሬጉላቶሪ አሰራር በተጨማሪ ተግባራዊ አለካክና የልኬት መሳሪያዎችን አጠቃቀምን እንዲረዱ ተደርገጓል፡፡ በመጨረሻም ከባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተርና የስራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር የማጠናቀቂያ ውይይት በማድረግ ትምህርታዊ ጉብኝቱ ተጠናቀቋል፡፡

  የኢትዮጵያ ጨረር መከላከያ ባለስልጣን ባዘጋጀው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ማቋቋሚያና የአሠራር መመሪያ ረቂቅ ሠነድ ላይ ከአገልግሎት ሠጪዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

  በውይይቱ መክፈቻ ላይ ስብሰባውን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ዑመር እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ከCategory 1 እና 2 ውጪ የሆኑ የጨረራ አመንጪዎች የጨረራ ደህንነትና ጥራት ፍተሻ (Radiation Safety Assessments) የሚያከናኑ ወይም የጨረራ ደህንነት ፣የጤና ፊዚክስን በተመለከተ የማማከር ሥራ ለሚያከናውኑ ለመንግስታዊና ለግል ድርጅት(ቶች) ተቋማት ወይም ግለሰብ(ቦች) ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ የሙያና የስነምግባር ግድፈቶችን ከፍትሀብሄርና የወንጀል ተጠያቂነት በመለስ የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ለመወሰን ባዘጋጀውና ተፈርሞ ወደስራ በገባበት የውል ሠነድ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀፅ(4) መሠረት ከውል ጋር በተያያዘና ተፈጻሚነቱን ለማሳለጥ በውሳኔ ላይ የሚቀርቡ የቴክኒክ ጉዳዮችን የሚመለከት አግባብነት ያለው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የማቋቋም እና አሰራሩንም የማሳወቅ ተግባርና ኃላፊነት የባለስልጣኑ ሆኖ መደንገጉን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው መመሪያው፡፡

  ለህብረተሰቡ ፣ ለተቋማትና ለግለሰብ ከአደጋ ነጻ የሆነ አካባቢ እንዲፈጠርላቸውና ደህንነታቸው የተረጋገጠ ለማድረግ፡፡

  በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ሰራተኞች የራድዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት ለመከላከል ፣ ከአደጋ ስጋት ነጻ በሆነ መልኩ አጋዥ በመሆን ለመንቀሳቀስ አዮን ፈጣሪ የሆኑ ጨረሮች አገልግሎት ላይ እየዋሉ የሚገኙባቸውን ድርጅቶች ፣ መ/ቤቶች ፣ የትምህርትና የምርምር ተቋማት ወዘተ የሚገኙበትን ልዪ ቦታ ቀድሞ የመጠቆምና የማሳወቅ መረጃ ለእሳት ድንገተኛ አደ/መከ/መቆ ባለስልጣን የመስጠት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደልብ በመዘዋወር ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በመከላከልና በመቆጣጠር የተቀናጀ አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ለማድረስ፡፡

  በ19 አንቀጾች ተጠቃሎ በቀረበው ረቂቅ ሠነድ ቅሬታ አቅራቢዎች የሚስተናገዱበትን ሥርዓት ከመነሻ እስከመድረሻ ያመላከተ ሲሆን የኮሚቴው አባላት የሚወከሉበት የስራ ክፍልን የሥራ ዘመናቸውና ቁጥራቸውን በተመለከተ በመመሪያው ክፍል 5 እና 6 በግልፅ አስፍሯል፡፡በዚሁ መሠረት በስብሰባው ላይ የተገኙት አገልግሎት ሰጪዎች ከረቂቅ ሰነዱ ጋር በያዘ ማብራሪያ ሊሰጥባቸው ወይም ማሻሻያ ሊደረብባቸው አለበለዚያም ሙሉ በሙሉ ሊወጡ ይገባል ያሉዋቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አንስተው ገንቢ ውይይት የተደረገ ሲሆን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከውይይቱ በተገኘው ግብዓት ረቂቅ ሠነዱን በማዳበር መመሪያ ፈጥኖ ሥራ ላይ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡

  መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የራዲዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ ተግባራትን ለማከናወን መግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

  የመግባቢያ ሥምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ሊከሰቱ የሚችሉት የእሳት እና የራዲዮሎጂካል/የኒውክለር አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ውድመት በመከላከልና በመቆጣጠር ከተጓዳኝ ጉዳት ለመጠበቅ በጋራ መስራትና ልማታዊ እድገት እንዲፋጠን ማስቻል ተቀዳሚ ተግባር ሆኖ መገኘቱ መሠረት የሚያደርግ ሲሆን የሚከተሉትን ጉዳዮችም ግብ አድርገዋል፡፡

  ለህብረተሰቡ ፣ ለተቋማትና ለግለሰብ ከአደጋ ነጻ የሆነ አካባቢ እንዲፈጠርላቸውና ደህንነታቸው የተረጋገጠ ለማድረግ፡፡

  በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ሰራተኞች የራድዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት ለመከላከል ፣ ከአደጋ ስጋት ነጻ በሆነ መልኩ አጋዥ በመሆን ለመንቀሳቀስ አዮን ፈጣሪ የሆኑ ጨረሮች አገልግሎት ላይ እየዋሉ የሚገኙባቸውን ድርጅቶች ፣ መ/ቤቶች ፣ የትምህርትና የምርምር ተቋማት ወዘተ የሚገኙበትን ልዪ ቦታ ቀድሞ የመጠቆምና የማሳወቅ መረጃ ለእሳት ድንገተኛ አደ/መከ/መቆ ባለስልጣን የመስጠት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደልብ በመዘዋወር ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በመከላከልና በመቆጣጠር የተቀናጀ አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ለማድረስ፡፡

  ሀገራዊ የራዲዮሎጂካል/የኒውክለር ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነትና ምላሽ ሥርዓትን ማጠናከር የሚቻለው ቡድኑን በመመስረት ብቻ ሳይሆን የስጋት ምንጭ ደረጃን መሰረት በማድረግ የቡድኑን አቅም በመሳሪያና በስልጠና መገንባት ፣ የምላሽ አቅሙን በተግባር ልምምድ በመፈተሸ ከተግባር ልምምድ የተገኙ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ጥንካሬዎቹ ይበልጥ እንዲጠናከሩ ፣ ድክመቶች እንዲታረሙ በተከታታይ በመስራት መሆኑን ሠነዶች ያረጋግጣሉ፡፡በመሆኑም የዝግጁነትና ምላሽ ቡድኑ ዘላቂነት እንዲኖረው በጋራ መግባቢያ ሠነዱ ላይ ዝርዝር ተግባራትን ለማከናወን በሁለቱም ወገኖች መረሃ ግብር በመቅረፅ የሚፈፀም መሆኑን ከማመልከት በተጨማሪ የሁለቱ መ/ቤት ኃላፊዎች በሰነዱ የተዘረዘሩት ተግባሮች ተፈፃሚነት በ6 ወር አንድ ጊዜ የሚገመግሙና በቀጣይም የተሻለ የአሰራር ስርዓት የሚዘረጋበትን ሁኔታ የሚያመቻቹበት ሁኔታና ለትግበራውም ያልተቋረጠ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ የሚኖርባቸው መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡

  ባለሥልጣኑ በቸርቸል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ የካቲት 6 እና 7/2006 ዓ.ም ባዘጋጀው ሥልጠና ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ ከ5 የክልል ዞኖችና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ታድመዋል፡፡

  የሥልጠናው ዋና ዓላማ ያተኮረው ጨረርና የኒኩሌየር ቴክኖሎጂ ለልማት ሲውል ጨረራ ባሁኑ ትውልድና በመጪው ትውልድ ላይ እንዲሁም በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም በጤናው ሴክተር ከተሰማሩ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መሥራት ለመከላከሉ ውጤታማነት የጎላ አስተዋጾ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡

  በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ጨረራ የሀገራችንን ልማት ለማፋጠን እጅግ ቁልፍ የሆነ የቴክኖሎጂ ውጤት እንደሆነ ገልፀው በአንፃሩ ግን ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሰውና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ጎኖች በርካታ እንደሆኑ ገልፀው እነዚሁም የጤና ባለሙያዎች ጨረራ በሰውና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጠንቆች ለመከላከል ከጤና ባለሙያዎች ብዙ እንደሚጠበቅ እና ከባለሥልጣኑ ጋር በትብብር መሥራት ወሳኝ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

  ሁለት ቀን በፈጀው ሥልጠና ላይ ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው ፁሁፎችና ገለፃዎች በባለሥልጣኑ ባለሙያዎች ተሰተዋል፡፡ ከነዚህም የጨረራ መሠረታዊ መርሆች ፣ የጨረራ አይነቶችና ተግባራቸው ፣ የጨረራ ሥነ-ህይወታዊ ጠንቆች ፣ የጨረራ ደህንነት መመሪያዎች ፣ የጨረራ አደጋና መንስኤ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎች ፣ የራዲዮሎጂና የኒውክሌር ህክምና በሚሉት እርዕሶች ዙሪያ የቀረቡ ፁሁፎች ናቸው፡፡ በቀረቡትም ፁሁፎች ዙሪያ የጤና ባለሙያዎቹ ላነሷቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከባለሥልጣኑ ባለሙያዎች በቂ ትንታኔና ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡

  በመጨረሻም በስልጠናው ማጠቃለያ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ጨረራ ለዘላቂ ልማታችን ስኬት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገንዝበን ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በመወጣት ደህንነት ባህላችንን (safety culture) ማዳበርና አጠናክሮ መቀጠል ለነገ የማይባል የቤት ሥራችን መሆኑን መረዳት ተገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ባለሥልጣኑ የቆመለትን ራዕይና ተልዕኮ በስኬት ከግቡ ለማድረስ ከባለድርሻ አካላት ብዙ እንደሚጠበቅ በማሳሰብ የዕለቱ የሥልጠና መርሀ-ግብር በስኬት ተጠናቋል፡፡

  አንድ ቀን በፈጀው ግምገማ ነክ ስልጠና ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ያለፈውን የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የባለሥልጣኑን ዕቅድ በሪፖርትታቸው ላይ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ እንደተገለፀው ባለሥልጣኑ ያከናወናቸው ጠንካራ ሥራዎችና የታዩ ደካማ ጐኖች በዝርዝር አቅርበው በተለይም መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃርና የሰው ሀይል የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ከማጠናከር አንፃር ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ ያጋጠሙት ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

  በሪፖርታቸው እንደገለፁት የ5 ዓመቱን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንደተቋምና እንደ ሀገር ለማሳካት ከሠራተኛውና ከአመራሩ የላቀ ሥራና ቁርጠኝነት እንደሚጠበቅ ታውቆ ለግቡ መሳካት የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሩ ደካማ ጐኖችን በማጥራትና ጠንካራ ጐኖችን የበለጠ በማጐልበት የቀጣይ 6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም በስኬት እንዲጠናቀቅ ጥሪያቸው ያስተላለፉ ሲሆን በቀረበው ሪፖርትም ላይ ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ዋና ዳይሬክተሩ እና ሌሎች የማናጅመንት አባላት ምላሽ ሰተዋል፡፡ በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ሲቪል ሰርቪሱን ተጠያቂነትና ግልፀኝነት የተላበሰ እንዲሆን መሥራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

  በስልጠና ነክ ግምገማው ላይ የታደሙት የባለሥልጣኑ ሰራተኞችና አመራሮች መንግስትና ህዝብ የሰጣቸው ኃላፊነት ለመዋጣት ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለመሥራት ቃል ገብተዋል፡፡

  ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን ተጠቅመው ሲቪል ሰርቪሱ የሚገኝበትን የለውጥ ሰራዊት የመፍጠር ዓላማ በስኬት ለማጠናቀቅ እንደሚተጉ የጋራ አቋም በመያዝ የዕለቱ የግምገማ ነክ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡

  በባለሥልጣኑ ስልጣን ተግባር መሰረት የተለያዩ የጨረራ አመንጪዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት ከሀገር ለማስወጣት፣ ለመጠቀም፣ ለመጓጓዝ ለማስተላለፍ ለማስወገድ ወዘተ.. ፈቃዶችን የሚሰጥ ተቋም ሲሆን የውል ስምምነት ከተለያዩ የጨረራ ደህንነት አገልግሎቶች የሚሰጡ የጨረራ ደህንነት ወይም የጤና ፊዚክስን በተመለከተ የማማከር ሥራ የሚያከናውኑ (Radiation Safety Assessments) የሚያከናውኑ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥር 01 2006 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡

  የውል ስምምነቱ ዓላማ በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት የጨረራ ማመንጨት መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑትንና በጨረራ አመንጪዎች ቅቡልነት ባገኘ ደረጃ ከአንደኛውና ሁለተኛው ክፍፍል (categorization) ውጪ ለሆኑ የጨረራ አመንጪ ቁሶችን መሳሪያዎችን በተመለከተ የጨረራ ደህንነትና ጥራት ፍተሻ የሚያከናውኑ ወይንም የጤና ፊዚክስ በተመለከተ የማማከር ስራ የሚያከናውኑ መንግስታዊና የግል ድርጅቶች ወይንም ግለሰቦች ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚኖርባቸውን የሀላፊነትና የተጠያቂነት ደረጃ በሚያመለክት መልኩ ግልፅ አሠራር በመዘርጋት እንደ የተግባሩ የወጣ የባለሥልጣኑ የቁጥጥር መስፈርቶች መሟላታቸው ለማረጋገጥ ነው፡፡

  የውል ስምምነቱን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣንን ወክለው አቶ አበደዱልራዛቅ ዑመር የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የፈረሙ ሲሆን 6 የጨረራ ደህንነትና ጥራት ፍተሻን ወክለው ዋና ሥራ አስኪያጆች ፈርመዋል፡፡

  በሳይንስና ቴክኖሎጂ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በታህሳስ 25/2006 ዓ.ም ባለሥልጣኑ ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ከ13 ማህበራት የተውጣጡ አመራሮችና ተወካዮቻቸው በታደመበት የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት 13ቱ የህዝብ ክንፎች ከጨረር መከላከያ ባለሥልጣን ጋር ዋነኛ ባለድርሻ አካላት ከመሆናቸውም ባሻገር ባለሥልጣኑ እያካሄደ ያለውን የጨረራ ቴክኖሎጂን ለአገራዊ ልማቱ ትርጉም ባለው መልኩ ለመጠቀምና ህብረተሰቡንና አካባቢውን ከጨረር አደጋ ለመከላከል በሚያደርገው ሁለገብ ጥረት ውስጥ የህዝብ ክንፎቹ ከባለሥልጣኑ ጋር በቅንጅት መሥራታቸው ለግቡ ስኬታማ መሆን የላቀ ሚና እንዳላቸው ከገለፁ በኋላ የህዝብ ክንፋ በሚደረጉት የጋራ ትብብር ስምምቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አጽዕኖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

  በተጨማሪም የባለሥልጣኑ መ/ቤት ከነዚህ የህዝብ ክንፍ አመራሮችና አባላቱ ጋር ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመፍጠር የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመጀመሪያ ተሰላፊዎች እንደሆኑ አበክረው ገልፀዋል፡፡ የህዝብ ክንፎቹም የባለሥልጣኑ መ/ቤት የሰጣቸውን ተልዕኮ በማስፈፀም የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳሬክተሩ በንግግራቸው ላይ እንዳሰመሩበት የህዝብ ክንፎቹ የራሳቸው የድርጊት መርሃ-ግብርና እቅዶቻቸውን በማስገባት ወደ ሥራ እንዲገቡ ባለሥልጣኑ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ማህበራቱ የሚገጥማቸውን ማናቸውንም ችግሮች አቅም በፈቀደ መጠን ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግም ገልፀውላቸዋል፡፡

  በውይይት መድረኩ ላይ ከየህዝብ ክንፋ የመጡ አመራሮችና ተወካዮቻቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አንስተው ሰፊና ጥልቅ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ በተለይም የቢሮ፣ የግብዓት፣ የሰው ሀይል ስልጠና በተመለከተ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተርና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች በቂ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ከማህበራቱ ጋር የተጀመሩ የጋራ የትብብር መስኮች በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥሉ ቃል በመግባት የዕለቱ የምክክር አውደ ጥናት በተሳካ መልኩ ተጠናቅል፡፡

  የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን በቸርችል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግማሽ ቀን የምክክር አውደ ጥናት ከሳይንስ ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በታህሳስ 17/2006 ዓ.ም አካሄደ፡፡

  በምክክር አውደ ጥናቱም ላይ ከሳይንስ ጋዜጠኞች ማህበር የተውጣጡ ከ20 በላይ ጋዜጠኞች የተሳተፉ ሲሆን የምክክር አውደ ጥናቱም ዋነኛ ዓላማ የኢትዮጵያ ጨረር መከላከያ ባለሥልጣን የጨረራ ቴክኖሎጂን ለዘላቂ ልማታችን ለመጠቀምና የጨረራ አመንጪ ቁሶች በህብረተሰቡና በአካባቢ ላይ የሚፈጥሩትን ጠንቆች ለመከላከል እንዲቻል በህብረተሰቡ ውስጥ የግንዛቤ መፍጠሪያ ዋነኛ መነሻ ሊሆን እንደሚችል እና የሳይንስ ጋዜጠኞች ማህበር አንዱ የባለሥልጣኑ አጋር በመሆኑ የጋራ የትብብር መስኮች ላይ በህብረት ለመስራት ትኩረት ያደረገ መሆኑን የመረጃና ህዝብ ግንኙነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ዙልፋ አብዶ ገልፀው ሁለገብ ትብብሩ እንደሚቀጥል በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አሳስበዋል፡፡

  በምክክር አውደ ጥናቱ ላይ ከባለሥልጣኑ የተጋበዙ ባለሙያዎች 4 ያክል ጨረር ተኮር የሆኑ የሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን የሚያሳዩ ፅሁፎችን ያቀረቡ ሲሆን ከቀረቡት ፅሁፎች መካከል የጨረራ መርሆችና ተያያዥ ፅንሰ ሀሳቦች ፣ የጨረራ ስነ-ሀይወታዊ ጠንቆች ፣ ራዲዮሎጂ ኒውክለር የሚያስከትለው አደጋና ክስተቶቹ ፣ የህዝብ ግነኙነት ሥራዎች የጨረር ህክምናን ከሚዲያ አንፃር እንዴት ማስፋፋት ይቻላል በሚሉት ርዕሶች ዙሪያ ጥልቅና ሰፊ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ የቀረቡትን ፁሁፎችንና ገለፃዎችን መነሻ በማድረግ ከሳይንስ ጋዜጠኞች ማህበር የተጋበዙ ጋዜጠኞችም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ በዋነኝነት የተነሳው ነጥብ ህብረተሰቡ ስለ ጨረራ አመንጪ ቁሶች ያለውን ግንዛቤ ለማዳበር ብዙ ርቀት መጓዝ እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል፡፡ ጋዜጠኞቹም ሞያቸው የሚጠይቀውን የባለሥልጣኑን መሥሪያ ቤት ከሚዲያ ጋር ለማገናኘትና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

  በምክክር አውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ልማት ላይ ከሚገኙት ሀገሮች አንዷ መሆኗን ጠቅሰው የጨረራ ቴክኖሎጂን በኢንዱስትሪ ፣ በኮንስትራክሽን፣ በማዕድን ልማት ፍለጋ ፣ በኒውክለር ህክምና ፣ በጥናትና ምርምር ስርፀት በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል ከመስኩ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች ትርጉም ባለው መልኩ ወደ ተግባር መለወጥ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ ያሰመሩበት ሲሆን ለዚሁ ስኬት እውን መሆን የሳይንስ ጋዜጠኞች ማህበር እና አባላቱ ከባለሥልጣኑ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አበክረው ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን ለማህበሩ አባላት የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ከማዘጋጀት አንስቶ በዕቅድ ዝግጅት ትግበራ እና ግምገማ አንዱ አጋዥ የህዝብ ክንፋችን ይሆናል በማለት ለማህበሩ አባላት አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የባለሥልጣኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ከማህበሩ ጋር በመረጃ ልውውጥ በጨረራ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤን በመፍጠር ያላሰለሱ ጥረቶችን እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት የዕለቱ የምክከር አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቋል፡፡

  በተፈጥሮ ስለሚገኙ የጨረራ አመንጪ ቁሶች(NORM – Naturally Occurring Radioactive Materials)

  ጨረራ አመንጪ ቁሶች ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ በተለያየ የአፈጣጠር አይነትና መጠን የሚገኙ ሲሆን ከምድር ውስጥ፣ በምድር ገጽ እና ከምድር ገጽ በላይ በጠጣር፣ በፈሳሽ እና በጋዝ መልክ ይገኛሉ፡፡

  ረዢም መንፈቀ ህይወት ያላቸው እንደ ዩራኒዬም፣ ቶሪዬም እና ፖታሲዬም እንዲሁም የነሱ ውጤት(ውልድ) የሆኑት እንደ ራዲዬምና ራዶን የተባሉት በተፈጥሮ የሚገኙ ጨረራ አመንጪ ቁሶች ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ቁሶች በምድር አለት እና ከባቢ አየር ውስጥ ምንጊዜም ይኖራሉ፡፡ የሰው ልጅም ምንም እንኳ ከነዚሁ በተፈጥሮ ከሚገኙ ጨረራ አመንጪዎች ቢጋለጥም የጨረራ ውስድ መጠኑ በጤናው ላይ ጉዳት ሳያስከትልበት አብሯቸው ይኖራል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ

  በተቀናጀ አለም አቀፋዊ ትስስር የኬሚካል፣የባውሎጅካል፣የራዲዮሎጅካልና ኒውክሌር ቁስና ኤጀንቶች አደጋን ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተቋቋመው የሲ.ቢ.አር.ኤ. ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንት በህብረቱ መቀመጫ ብራስልስ፣ቤልጅየም ከኦክቶበር 28 እስከ 31 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ አብዱረዛቅ ኡመር፣የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀገሪቱ የቀረበላት ግብዣ መሰረት ተሳትፎ አድርገው መመለሳቸውን ሪፖርታቸው ያመለክታል፡፡ የጉባኤው አላማ አባል ሀገራቱን ማስፋትና በሀገራቱ መካከል ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ሆኖ ባከናወናቸው ተግባራት ላይ በመወያየት፣የተሻለ ተሞክሮ መቅሰምና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ

  በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን የማሳወቅና ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት በጊቤ 3 ለሚገኙ ኒውክለር ዴንሲቲ ጌጅ ተጠቃሚ ባለሙያዎች ከጥቅምት 9-11 ቀን 2006ዓ.ም የጨረራ ደህንነትና ቁጥጥር በሚል ርእስ ከኒውክለር ዴንሲቲ አንጻር ስልጠና ሰጡ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ

  ኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን በህዝብ ክንፍነት ከለያቸው የተደራጁ 13 በማህበር ከተደራጁ አካላት ተወካዮች ጋር መስከረም 30 ቀን 2006ዓ.ም በቲዲኤስ ሆቴል፣አዲስ አበባ ፣ኢትዮጵያ የግማሽ ቀን የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡የመድረኩ የተዘጋጀው ባለስልጣኑ ከህዝብ ክንፍ ጋር በሚያገናኛቸው መስመር ላይ ተልእኮ በመሰጣጣት የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ሲሆን አላማው በሀገራችን ጨረራ ለልማት በሰፊው እንዲውልና ሰውና አካባቢ ከጨረራ ጠንቅ ተጠብቆ ማየት ነው፡

  ተጨማሪ ያንብቡ

  በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን፣የኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈጸም ዳሬክቶሬት ከብረት አስመጭና አቅላጭ ድርጅቶች ጋር “የብረት የጨረር ብክለትና መደረግ የሚገባው ጥንቃቄ”በሚል ርእስ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ውይይት በአምባሳደር ሆቴል አካሄደ፡፡የውይይቱ አላማ ተቋማቱ ከጨረር ብክለት የጸዱ ብረቶችን እንዲያስመጡና እንዲያቀልጡ አስፈላጊውን ግንዛቤ በመስጠት ሰራተኞቻቸውን፣የምርቶቻቸው ተጠቃሚውን ህብረተሰብና አካባቢን ከጨረራ ብክለት መጠበቅ ማስቻል ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ

  በሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር በክብርት ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የተመራ አምስት አባላትን ያካተተ ልኡካን ከመስከረም 6 እስከ 10 ቀን 2006ዓ.ም በአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ “የጨረራና ኒውክለር ቴክኖሎጅን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋል በሚደረግ በአለም አቀፋዊ የውይይትና የምክክር መድረክ” በመገኘት በጋራና በጠናጥል ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ተመልሰዋል፡፡

  የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በሪፖርታቸው እንዳመለከቱት በተለይም በአፍሪካ የኒውክለር ሬጉላቶሪ አካላት ፎረም ( The Forum of Nuclear Regulatory Bodies in Africa or FNRBA)፣ከፍተኛ ሬጉላቶሪዎች የውይይት መደረክን ተሳትፎን (Senior Regulators Meeting ) እና አጠቃላይ የኒውክለር ፍተሻ እገዳ ስምምነት (Comprehensive Nuclear Test Ban Treaty Organzion or CTBTO) በተመለከተ በርካታ ጠቃሚ ውይይቶችና የጋራ መግባባቶች ተደርገዋል፡፡

  በአፍሪካ የኒውክለር ሬጉላቶሪ አካላት ፎረም (FNRBA) በአፍሪካ የሬጉላቶሪ አካላት የጨረራ መከላከል፣የኒውክለር ጥበቃና ደህንነት፣የሬጉላቶሪ መሰረተ መዋቅር የሚስፋፋበትና የሚጠናከርበት ምቹ ሁኔታና ፖሊሲ ዘርግቶ የሚንቀሳቀስ እ.ኤ.አ መጋቢት 9 ቀን 2009ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ አህጉራዊ ድርጅት ነው፡፡ፎረሙ ባለፉት አራት አመታት በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን አቅሙን ለማሳደግ ከአሜሪካ ኒውክለር ሬጉላቶሪ ኮምሽን፣ከኮሪያ የኒውክለር ሴፍቲ ኢንስቲትዪትና ከአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ ጋር የትብብርና ድጋፍ ስምምነቶችና ማድረጉ ይጠቀሳል፡፡በዚህም ጉባኤ ፎረሙ ኤጀንሲው ሆነ ከሌሎች አገሮች ድጋፍ ማግኘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ እራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ መቀጠል እንደሚገባው፣አባል ሀገራቱ በድረ ገጹ የመረጃ ልውውጥ ማጠናከር እንደሚገባቸው፣እና በአፍሪካ ህብረት እንዲደገፍ የሚሉት ሀሳቦች በዋናናነት ተነስተዋል፡፡

  ሲኒየር የሬጉላቶሪ አካላት መሪዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፎ ባደረጉበት መድረክ የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ከማሌዥያና ኢንዶኔዥያ የሬጉላቶሪ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት መጣርና የደረሱበት አኮኖሚያዊ ደረጃ ለመድረስ መሞከር፣ከጨረራና ኑክለር ቴክኖሎጅ ለሰላማዊ ልማት ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ለቴክኖሎጅ ሽግግር በቅድሚያ ሁኔታነት በአደጉ ሀገራት የሚቀርቡ ስምምነቶች ላይ ጥልቅ ጥናት ማካሄድ እንዲቻል በዘርፉ ለመተባበርና ድጋፍን ለማድረግ ስምምነቱን ከገለጸው ተቀማጭነቱ በእንግልዝ ከሆነው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት VERTIC ጋር በጋራ መስራት የሚሉትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫነት ይዟቸዋል፡፡

  አጠቃላይ የኒውክለር ፍተሻ እገዳ ስምምነት በሚከታተለው CTBTO ከተደረገው የስራ ጉብኝት በመነሳት የባለስልጣኑ የትኩረት አቅጣጫ ሀገራችን ከምትከተለው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጅ በተጨማሪ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ኢኖቬሽን ፖሊሲ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ፕሮግራም የተቀረጸለት በመሆኑ በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ክስተቶችን በንቃት ለመከታተል እንደ ሴስሚክ ጣቢያና ዳታ ሴንተር ሁሉ የራዲዮኒኩላይድ መከታተያና መተንተኛ ላቦራቶሪ የሚደራጅበት ሁኔታ መፍጠር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን ተብራርቷል፡፡

  በድሬዳዋ የምክክር መድረክ ተካሄደ የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን ለሀረሬ፣ ጅጅጋና ድሬዳዋ ፍትህ አካላት uድሬዳዋ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

  ባለሥልጣኑ ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በድሬደዋ ሰላም ብሉ በርድ ሆቴል የተካሄደው የምክክር መድረክ የተሻሻለው አዋጅ ላይ ያተከረ ነው፡፡

  በዚሁ ዕለት 27 ተሳታፊዎት ተካፋይ የሆኑ ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው፡፡

  በድሬደዋ ከተማ የተካሄደው መድረክ የጨረራ ጥቅምና ጉዳት ላይ ስፉ ያለ ገለፃ የተካሄደ ሲሆን የባለሥልጣኑን አዋጅ በድጋሚ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ያስፈለገውን ለምንድን ነው? የኑክለር ህግ የተለየ የህግ ተዋረዶችና የኑክለር ህግ ቁጥጥር ተግባራት በዕለቱ ተዳሰዋል፡፡

  የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል የአፍሪካ ሀገራት የጨረራና የኒውክለር ተቆጣጣሪ ተቋቋማት ጠንካራ የጨረራ ቁጥጥር መሰረተ ልማት እንዲኖራቸው የሚረዳ አህጉራዊ ስልጠና “Regional Training Course for Regulators on Authorization and Inspection of Radioactive Source, From 26Aug to 20 Sep 2013“ በሚል ርእስ ከ25 የአፍሪካ ሀገራት ለተወጣጡ የጨረራ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ከአሜሪካ፣ከጋና፣ከኦስትሪያ፣ከናይጄሪያና ከኢትዮጵያ በተወጣጡ በመስኩ ከፍተኛ ትምህርትና ልምድ ባላቸው ምሁራን በቲዎሪና በተግባር የታገዘ ስልጠና አለም አቀፍ ኦቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ ድጋፍ በኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን አስተባባሪነት በኢትዮጵያ አምባሳደር ሆቴል በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

  ዶር ኢብራሂም ሻዳድ፣ በአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲ የአፍሪካ አስተባባሪ፣የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጅ ኤጀንሲን መልእክት ሲገልጹ ኢትዮጵያ ለዚህ ስልጠና መመረጥዋ ሀገሪቷ ያላትን ጠንካራ ትስስርና ቁርጠኛነት የሚያሳይ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ በሀገሪቷ የጨረራና ኒውክለር ቴክኖሎጅ ለሰላማዊ አገልግሎት እንዲውል ከፍተኛ የሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት በመስኩ እንዲኖራት እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡አያይዘውም ኤጀንሲው ለአፍሪካ አባል ሀገራት ከፍተኛ የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንና ይህም የጨረርና የኒውክለር ትክኖሎጅ ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ በማዋል ሰውና አካባቢ በተጓዳኝ የጨረራ ጠንቅ እንዳይጎዱ የመከላልና የመቆጣጠር ተግባራትን በእጅጉ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡በተለይም ጨረራ ለሰላማዊ አገልግሎት እንዲውል የኤጀንሲው ዘመኑ የደረሰበትን የትግበራ ማኑዋሎች በየጊዜው በማዘጋጀት በአባል ሀገራት ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የጨረራ መሰረተ ልማቶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አስገፈላጊውን ስልጠናና ደጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህ ስልጠናም በህክምናና በእንዳስትሪው ዘርፍ የተፈበረኩትን የጨረራና የኒውክለር ቴክኖሎጅ በተግባርና በቲዎሪ ለጨረራ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት በቀጣይ በመስኩ በቂ የቁጥጥር ተግባራትን እንዲያከናውኑ ክህሎታችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

  ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚንስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ደሚቱ አለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ለዚህ አህጉራዊ ስልጠና ኢትዮጵያን በመምረጣቸው አድናቆታቸውን ገልጸው ይህ አህጉራዊ ስልጠና ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጅ መስክ ብሎም በጨረራና ኒውክለር ቴክኖሎጅ አያሳየች ያለውን ፈጣን እድገት አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጅ የሰለጠ የሰው ሀይል መኖሩ ወሳን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  ጨረራ በሀገራች በግብርናው፣በህክምናው፣በኢንዳስትሪው፣በኮንስትራክሽን፣በምርምር ዘርፍ፣ወዘተ አየሰጠ ያለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ከእለት ወደ እለት አያደገ መምጣቱን ገልጸው በመስኩ የሰለጠነ የሰው ሀይል መኖር የቁጥጥር ተግባራቱ የተሳለጠ እንዲሆን ይህ አህጉራዊ ስልጠና መዘጋጀቱ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልረዛቅ ኡመር አስረድተዋል፡፡

  እንግዶቹ በቆይታቸው የመጀመሪያ ሳምንት ሀገራችን የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት ዘመቻ ከማስተዋወቅ አንጻር የችግኝ ተከላ ያካሄዱ ሲሆን በተጨማሪ ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የአፍሪካ ህብረት ጎብኝተዋል፡፡በቀጣይም በልዩ ልዩ ኢንዳስትሪዎችና የህክምና ተቋማት የጨረራ ተግባራትን በተግባር ትምህርት ይቀስማሉ፡፡

  ሰሞኑን አንዲት ቻይናዊት ለ 40 ደቂቃ በአይፎን በማውራቷ ሞባይሉ ፈንድቶ ከፍተኛ ጉዳት ያደርስባታል ይህን ተከትሎ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣንን ማብራሪያ በመጠየቃቸው በዚህ ጣቢያ ላይ ማብራሪያ በመጠየቁ ባለስልጣኑ ይህን አስመልክቶ ማብራራ ሰጥቶ ነበር ፡ነገር ግን የተሰጠው ማብራሪያ ሰፊና በቂ ስላልነበር ይመላል ከብዙ ሰዎች የስልክ የተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄዎችን ባለስልጣኑ ተብሏል፡፡ለበለጠ መረጃ ግን ሞባይል ስልክ ከጨረራ ጋር ያለውን ተዛምዶ በተመለከተ በስልክ ለጠየቃችሁ ሁሉ ለበለጠ መረጃ ይረዳችሁ ዘንድ እነሆ ትንሽ ስለጨረራና እና ሞባይል ስልክ ተዛምዶ ትንሽ እንበላችሁ፡፡

  ጨረራ በሁለት ይከፈላል

  1. አየን ፈጣሪ (Ionizations Radiation)
  2. ይህ የጨረራ አይነት በከፍተኛ የሀይል ምንጭነት የሚታወቅ የጨረራ አይነት ሲሆን ይህ የጨረራ አይነት ከሰዎች ከአከባቢና ከሌሎች ቁሶች ጋራ መስተጋብር ሲፈጥር ወይም በእነዚህ ቁሶች ውስጥ ሲያልፍ ሀየን መፍጠር የሚችል ከመሆኑም በተጨማሪ በሰዎችና በእንስሳት እዋሶች ውስጥ ሲያል እንደ ጨረራው አይነትና ዶዝ መጠን የተለያ ጉዳቶችን በእዋሶቶቻቸውና በአካላቶቻቸው ላይ በአይን ሊታይ የሚችልና ሊታይ የማይችል ጉዳቶችን (visible and Invisible Effects) ሊያደርስ ይችላል፡፡እንደዚህ አይነት ጨረራን የሚያወጡ መሳሪያዎች በአገራችን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በህክምናው (ኤክስ ሬይ፣ሲቲ ፣ማሞግራፊና፣የጥርስ ራጅ ዴንታል) በኮንስትራክስን ዘርፍ( ኒውክላር ዴንሲቲ ጌጄ)፣በኢንዱስትሪው ለብረታብረት ምርት ጥራት ማረጋገጫ ስራ፣ በግብርናው ዘርፍ ለተለያዩ ምርጥ ዘሮችን ለማግኘት ለሚያስችል ምርምር ስራ በሰፊው ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡በመሆኑም እኚህን አየን ፈጣሪ የሆኑ የጨረራ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ተቋማት በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋሉት በአከባቢና በህብረተሰብ ላይ ተጓዳኝ ጉዳት ሊያደሱ ስለሚችል በፈቃድ ብቻ እንዲሰሩ ከመደረጉም በላይ በየጊዜው ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡

  3. አየን ፈጣሪ ያልሆነ ጨረራ(Non-Ionzation Radiation)
  4. ይህ የጨረራ አይነት በሰውነት ውስጥ ቢያልፍም በእዋሶቻችን ላይ ሙቀት ከመጨመር ውጪ አየን የመፍጠር አቅም የሌለው የጨረራ አይነት ነው፡፡ይህም የጨረራ አይነት በዓለማችንና በሀገራች በተለያዩ ዘርፎች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ፎቶኮፒ ማሽኖች፣ሞባይሎች የቴሌ የሳተላይት መረጃ መቀበያዎች፣ አልትራ ሳውንድ ፣ለማብሰያ አገልግሎት የሚውሉ ኦቨኖች(Oven) የጸጉር ማስተካከያ ማሽኖች ከብዙዎቹ ሊጠቀሱ የሚችሉት ናቸው ፡፡

  ስለሆነም የሞባይል ስልክ አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ስሪት ከጨረራ ልቀት አንጻር የሚያወጣው ጨረር አየን ፈጣሪ ባለመሆኑ የጆሮ ታንቡር ሙቀት ከመጨመሩ ውጪ ሊያመጣ የሚችለው የጨረራ ተጓዳኝ ጉዳት ሞባይል ለመጠቀም ስጋት ውስጥ የሚከተን አይደለም፡፡ሰሞኑን ቢቢሲ የዘገበው የቻይናዊቷ ሴት ጉዳት ግን ተጨማሪ ጥናት የሚጠይቅና መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የማያስችል መሆኑ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡የአሜሪካ የዘርፉ ተመራማሪዎች በሞባይል ስልክና በአይን ፈጣሪ ባልሆኑ ማሳሪያዎች ተጓዳኝ ጉዳት መጠንና ጠንቁ ቀምረው በትክክል ለማስቀመጥ ቢያንስ የአምስት ዓመት ጥናት እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ የሞባይል ጨረራና ተጓኝ ጉዳቱን ውጤቶችን በወቅቱ ሊያሳውቅ እንደሚችል እየገለጸ የሚኖሩት አዳዲስ ግኝቶችና ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን በወቅቱ እንደምንገልጽ እንገልጻለን፡፡

  1. ለረጂም ሰዓት በሞባይል ስልክ ባያወሩ ከተቻለና አሳብ በቀላሉ መግለጽ ከተቻሉ በኤስ ኤም ኤስ ማስተላፍ ቢችሉ መልካም ስለሆነ ይህንን በማድረግ ሊወሰድ የሚችለውን የጨረራ መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡

  2. የግድ ካልሆነ መስጠቀር በቢሮ ውስጥ ወይም ቤት ውስጥ ከሆኑ የመስመር ስልክ መጠቀም ቢቻል የተሻለ ይሆናል፡፡

  3. በቢዝነስ ጉዳይ ብዙ ሰዓት ለሚያወሩ ሰዎች ኤር ፎን (Air phone) ቢጠቀሙ፡፡ይህም በቀላሉ በጣም ስስ ለሆነው የጆሮ ታምቡደር ቅርብ ሆኖ በቀላሉ እንዳይጠቃ ርቀትን በመቀነስ ሊወሰድ የሚቻለውን የጨረራ ውስድ መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡የጨረራ መከላከል መመሪያዎች ውስጥ አንደኛው ርቀትን መጨመር ስለሆነ ርቀትን በጨመርን ቁጥር የውስድ መጠንን መቀነስ እንችላለን፡፡

  4. የሞባይል ስልኩን ኪስ ውስጥ ባይቀመጥ ወይም በያዙበት ወቅት ከሰውነት አካሎት ጋር መነካካት እንዳይችል አድርጎ ማስቀመጥ ቢቻል ይመከራል፡፡ይህም የሞባይሉ ሬዲዮ ሞገድ ከዋናው ሰርቨር ጋር ለመገናኘት በሚያደርገው ጥረት ቢያንስ አንድ ፐልስ በሰከንድ ይቀበላል፡፡ይህን ግንኙነት ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት የሚፈጠረውን የጨረራ መጋለጥ መቀነስ ይቻላልና፡፡

  5. የህጻናት የሴሎቻቸው የዕድገት ስርጭት ፈጣን ከመሆኑም በላይ ከአዋቂ ይልቅ ስስ ስለሆነ በቀላሉ በሞባይል ስልክ ጨረራ የመጋለጥና የመጎዳት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ስለዚህ ህጻናት በሞባይል ስልክ እንዳይጠቀሙ እንዲደረግ አጥብቆ ይመከራል፡፡

  በስተመጨረሻ ለሞባይል ስልክ አጠቃቀም ጋር ለህብረተሰቡ በዘንጋት የሌለበት ነገር ሞባይል ቻርጅ ላይ ሰክተው ስልክ ለረጅም ሰዓት ባያወሩ እንደሚመረጥ በጥብቅ ለመምከር እንወዳለን፡፡


  የጨረራ ቪድዮ

  የኢ.ጨ.መ.ባ 2005 ዶክመንተር ቪድዮ.

  በማህበራዊ ድረገጻችን ይጎብኙን


  Your Feed back

  Detail address