Latest News Latest News

Back

የቼርኖቤል ጦስ ክፍል-1

ትርጉም፡- ታደለ ነጋሽ  (ከኢጨመባ)

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 26 ቀን 1986 ዓ.ም፡፡ በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አንድ ክፍል በነበረችው በዩክሬይን ውስጥ ቼርኖቤል በተባለ ቦታ ተቀራርበው ከሚገኙ 4 የኑክሌር ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ውስጥ በአንደኛው ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከሰተ፡፡ ይሄው ፍንዳታ የደረሰበት ጣቢያ ለጥገና ተብሎ ማመንጨት ከሚችለው ሀይል 10 በመቶ ብቻ ለጥገናው ስራ እየተጠቀመ ነበር፡፡ የተከሰተው ፍንዳታ ለአስር ቀናት ያክል የተለያዩ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ አደገኛ ጨረራ አመንጭ ቁሶች ራዲዮኑክላይዶች በአየር ላይ እንዲበተን እና እንዲቀላቀል ያስገደደ ነበር፡፡ ይሄው ክስተት ከፍተኛ የአየር ብክለት አስከተለ፡፡  ብክለቱም በዚያው አካባቢ ብቻ ሳይወሰን በነፋስ አጋዥነት አውሮፓን እና ሌሎች አካባቢዎችን አዳረሰ፡፡

በወቅቱ በነበረው የአካባቢው ዝናባማ የአየር ንብረት አማካኝነት እነዚሁ አየሩን የበከሉ ብናኞች ወደ መሬት ላይ ከዝናቡ ጋር ተቀላቅለው አብዛኛውን ቦታ ሳያዳርሱ በተወሰነ አካባቢ ላይ በማረፍ ሊጠራቀሙ አስቻለ፡፡

በፍንዳታው ወቅት ከጣቢያው አፈትልከው ከወጡት እና ያካባቢውን ህዝብ ለጨረራ ሊያጋልጡት ከሚችሉት ውስጥ  አዮዲን - 131፣ ሲዚየም - 134  እና ሲዚየም - 137 ይገኙበታል፡፡ አብዛኛውም በውጫዊ መጋለጥ ከፍተኛ የጨረራ ውስድ እንዲኖር ያስገደደው በመሬት ላይ በተከማቸው እና እየተነነ በምንተነፍስበት ጊዜ ወደ ውስጥ በመግባት ጉሮሮን እና ሳንባን የሚያጋልጠው  አዮዲን - 131 ሲሆን በራዲዮኑክላይድ በተበከለ ምግብ አማካይነትም ውስጣዊ መጋለጥ ነበር

ይሄው በሀይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የደረሰ አደጋ ያስከተለው የጥፋቱ መአት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ለከፍተኛ ጨረራ ከማጋለጡም ባሻገር ለ31 ሰዎች ሞትን አስከተለ፡፡ ከሟቾቹም ውስጥ 28ቱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ነበሩ፡፡  እነዚሁ ሟቾች በመሬት ላይ ከተከማቸው ቁስ በሚፈተለክ ቤታ በተባለ ጨረራ   ከ3  እስከ  16 ሚሊ ሲቨርት ከመጋለጣቸው ባሻገር ሰውነታቸው በመበከሉም ለከፍተኛ የቆዳ ህመም ዳረጋቸው፡፡ በተጨማሪም  209  ሰዎች ለሆስፒታል ተዳርገው በተደረገላቸው ምርመራ 106 ያህሉ ጊዚያዊ እና ቀላል ህመም ቢታይባቸውም ባጋጣሚ ሁሉም አገግመው ከጥቂት ሳምንታት እስከ ወራት በፈጀ ጊዜ ወደ ቤታቸው ለመመለስ በቅተዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ  ከ100,000 ሰዎች በላይ አካባቢውን እንዲለቁና በቤላሩስ፣ በዩክሬይን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ቦታዎች እንዲሰፍሩ ተገደዋል፡፡

አካባቢውም በከፍተኛ ደረጃ ማንም እንዳይገባበት ተከለለ፡፡  የቼርኖቤል ሪአክተርን እና አካባቢውን የማጽዳት ስራ የተከናወነ ሲሆን ለዚሁም ስራ ከ750,000 በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ነበር፡፡  ከነዚህ የተበከሉ ነገሮችን ሲያጸዱ ከነበሩት ውስጥ የተወሰኑት ዓለም አቀፉ የጨረራ መከላከያ ተቋም ካስቀመጠው የጨረራ ውስድ መጠን ወሰን  50ሚሊ ሲቨርት በላይ በማለፍ እሰከ  165ሚሊ ሲቨርት  ድረስ ለመጋለጥ የቻሉ ሲሆን በእንደዚህ አይነት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ተቋሙ አንድ ሰራተኛ  ከ 500ሚሊ ሲቨርት በላይ እንዳይጋለጥ ይመክራል፡፡  ይህም በጨረራ ስራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በአጭር ጊዜ ለሚታዩ ህመሞች እንዳይዳረጉ ይረዳል፡፡ ለዚህም በየጊዜው የሚኖረውን መጋለጥ መጠን ሊመዘገብ ይገባል፡፡  ይህንን የሚሰራው ተቆጣጣሪ ቡድንም በየጊዜው ሲለካ ከመዘገበው መረጃ ለማየት እንደተቻለው አደጋው በተፈጠረበት የመጀመሪያ አመት የመጋለጥ መጠኑ  ከ165 ሚሊሲቨርት በታች ሆኖ የቆየና በተከታታይ አመታትም ወደ 50 ሚሊሲቨርት ወርዷል፡፡

ከአደጋው ቀጥሎ የጤና ጉዳቶች ይመጣሉ ብሎ በመጠርጠር በቤላሩስና በዩክሬይን ዙሪያ ባሉት አካባቢዎች ከፍተኛ እና እልህ አሰስጨራሽ የሆነ ጥናት ተካሄደ፡፡  በዚህም ላቅ ያለ ጉዳት የገጠማቸው በቤላሩስ እና ዩክሬይን ያሉ ህጻናት ላይ ሲሆን መንስዔውም በአዮዲን-131 የተበከለ ወተት የጠጡ ሆነው ተገኙ፡፡

(ክፍል ሁለት ይቀጥላል)

አደጋ የደረሰበት የቼርኖቤል ኑክሌር ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ውስጥ አንደኛው

              

ምንጭ፡- ከኢንተርኔት እና ኢንሳይክሎፒዲያ

Your feedback Your feedback

Suggestions

Your input is valuable to us. Please send us your suggestions.

This field is mandatory.
This field is mandatory.

Play to see ERPA video Play to see ERPA video

Workshop on Radiation Safety and Security conducted Workshop on Radiation Safety and Security conducted

A workshop organized by the National Nuclear Security Administration of U.S in cooperation with the Ethiopian Radiation Protection Authority was conducted at Hilton Hotel, Addis Ababa, from August 3 to 4, 2015. The workshop focused on the development of regulations that is a vital tool for the security of radioactive sources and nuclear facilities. Specific topics such as IAEA Code of conduct which basically provides guidance for developing policies laws and regulations to uphold the safety and security of radioactive sources, categorization of radioactive sources that helps maintain a high level of safety and security, IAEA Nuclear Security Series that serves as a guidance for establishing regulating requirements, regulatory development process that introduces a systematic process which helps make development of new security regulations more effective and efficient and principles that highlight effective regulation drafting were critically addressed in the workshop.

Read More

Menu Menu