Latest News Latest News

Back

የቼርኖቤል ጦስ ክፍል 2

ታደለ ነ. (ኢ.ጨ.መ.ባ)

አዮዲን-131 የተባለው ጨረራ አመንጭ ቁስ ጨረራ የማመንጨት ችሎታው በግማሽ የሚቀንስበት መንፈቀ ህይወቱ 8 ቀናት የሆነው በእንቅርት ውስጥ የሚከማች ከሆነ በህጻናት ላይ የሚያስከትለው ችግር ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ቼርኖቤል ያስከተለውን ውጤት የተባበሩት መንግስታት ኤስ.ሲ.ኢ.ኤ.አር በ2000 አትሙ አውጥቶታል፡፡ ይሄው ሳይንሳዊ ፍተሻ  እንደሚሳየው በአደጋው ወቅት ከተጋለጡት ውስጥ 1800 ለእንቅርት ካንሰር የተዳረጉ ህጻናት እንደሚገኙበት ያሳያል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ከፈጠረው በርካታ  ጉዳቶች አንጻር ከፍተኛ ህመም ቢኖርም ለሞት የዳረገ አልነበረም፡፡ ከጦሱ ጋር በተገናኘም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘም ፡፡

ሌላው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የታዩ የጤና ችግሮች ጭንቀት፣ ውጥረትና የጨረራ ፍራቻ ይገኙበታል፡፡እንደ ድርጅቱ አገላለጽ ከሆነ በከፍተኛ ደረጃ ተጋልጠው ከነበሩት ውጭ ሌሎቹ አብዛኞቹ በወደፊት ህይወታቸው ላይ ለከፋ የጤና ጉዳት የመዳረግ እድላቸው የመነመነ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡

እንደ እስካንዲኔቪያ የመሳሰሉት የአውሮፓ ክፍሎችም ከአደጋው ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው ሳምንት አካባቢ በርካታ ሰዎች እስከ 0.1ሚሊሲቨርት ድረስ ተጋልጠው ለራስ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስቀመጥና የቆዳ መለብለብ ገጥሟቸው ወደ ህክምና መሄዳቸው ታውቋል፡፡

ለአንድ ምዕተ አመት ያህል ጨረራ የሚያስከትለው ተጽእኖ ላይ ጥናቶች እንዳመለከቱት እንደዚህ ያለ አነስተኛ የጨረራ ውስድ መጠን የተከሰተውን አይነት ችግር በቀጥታ ማምጣት እንደማይችል ነው፡፡

ይሁን እንጂ የቼርኖቤል ጦስ ከሰጣቸው ትምህርቶች አንዱ በብዙዎች ዘንድ ጨረራ መፈራቱ ነው፡፡ በወቅቱም 20በመቶ የሚሆኑ የቤላሩስ እርሻዎች ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎቹ እንዲዘጉ ቢወስንም ሀገሪቱ በገጠማት የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት ምክንያት ለተወሰኑ አመታት ሀይል የመስጠት አገልግሎቱ እንደቀጠለና እ.ኤ.አ 1991 ላይ በአንደኛው ሀይል ማመንጫ ላይ ባጋጠመ መጠነኛ የእሳት አደጋ ምክንያት የበለጸጉት አገራት መልሶ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት ካላቸው ስጋት የተነሳ ከዩክሬይን መንግስት ጋር በመግባባትና በለገሱት 300 ሚሊየን ዶላር አማካኝነት በ2000ዓ.ም ላይ ቀሪዎቹን ሪአክተሮች ሙሉ በሙሉ በመዝጋት አገልግሎት መስጠት እንዲያቋርጡ ተደርጓል፡፡

ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬ ላይ ቸርኖቤል በ30 ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ በጥብቅ የተከለለ ዞን ሲሆን ሰው እንዳይኖርበት የተደረገ ቢሆንም ቱሪስቶች ከዋና ከተማዋ ኪየቭ በስተሰሜን የሁለት ሰዓት ጉዞ በቱሪስቶች መጓጓዣ ብቻ በመጠቀም መጎብኘታቸውን ወደኋላ አላሉም፡፡ በዚህ የተከለለ ዞን ውስጥ ሆቴሎች ይገኛሉ፡፡ ጎብኚዎችም በመቆጣጠሪያ ጣቢያ ትዕዛዝ እና በአስጎብኚዎች ብቻ እንዲመሩ ግድ ሆኗል፡፡ 


Your feedback Your feedback

Suggestions

Your input is valuable to us. Please send us your suggestions.

This field is mandatory.
This field is mandatory.

Play to see ERPA video Play to see ERPA video

Workshop on Radiation Safety and Security conducted Workshop on Radiation Safety and Security conducted

A workshop organized by the National Nuclear Security Administration of U.S in cooperation with the Ethiopian Radiation Protection Authority was conducted at Hilton Hotel, Addis Ababa, from August 3 to 4, 2015. The workshop focused on the development of regulations that is a vital tool for the security of radioactive sources and nuclear facilities. Specific topics such as IAEA Code of conduct which basically provides guidance for developing policies laws and regulations to uphold the safety and security of radioactive sources, categorization of radioactive sources that helps maintain a high level of safety and security, IAEA Nuclear Security Series that serves as a guidance for establishing regulating requirements, regulatory development process that introduces a systematic process which helps make development of new security regulations more effective and efficient and principles that highlight effective regulation drafting were critically addressed in the workshop.

Read More

Menu Menu