ተግባራዊ መደረግ የሚገባቸው የጨረራ መከላከያ ዘዴዎች ተግባራዊ መደረግ የሚገባቸው የጨረራ መከላከያ ዘዴዎች

Return to Full Page

በየአለምዓቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ባስቀመጠው እስታንደርድ መሠረት ማንኛውም ሰው ሊተገብራቸው የሚገባ 3 ዋና ዋና የጨረራ መከላከያ ዘዴዎች አሉ፡፡ እነዚህም

 

  1. ጊዜ ወይም/Time/
  2. ርቀት ወይም/Distance/
  3. ከለላ መጠቀም ወይም / Shieding /ናቸው፡፡

 

 

  • ጊዜ ስንል ማንኛውም ሰው የጨረራ ቁሶች ባሉበት አካባቢ የቆይታ ጊዜውን በጣም ማሳጠር ካልቻለ ለጨረራ የመጋለጥ እድሉ ይሠፋል፡፡ ስለዚህ የጨረራ ቁስ ባለበት አካባቢ ቆይታውን በማሳጠር መከላከል ይቻላል፡፡

 

 

  • ርቀት ወይም /distance/የጨረራ ቁሶች በተከማቹበትና እንዲሁም የራጅ ክፍሎች የኤክስሬ ማሽን በተግባር ስንጠቀም ከአካባቢው ካራቅን በጨረር የመጋለጥ እድላችን በእጥፍ ይጨምራል፡፡ በአንፃሩ የጨረራ ቁሶቹ ካሉበት አካባቢ እየራቅን በሄድን ቁጥር ተጋላጭነታችን ይቀንሣል፡፡

 

 

  • ከለላ ወይም /Shielding/ማንኛውም ሰው የጨረራ ቁሶችን ደረጃቸውን በጠበቁ ከለላዎች መሸፈን ይኖርባቸዋል፡፡

 

በተለይም የራጅ ክፍሎች ሲገነቡ በአለምዓቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ የጨረራ ደህንነት መሥፈርቶች ማሟላታቸውን በየጊዜው መከታተል አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ራዲዮግራፈሮች የክሊኒክ ባለቤቶች ለገንዘብ ማስገኛ ሲሉ ደጋግመው ህብረተሰቡን ራጅ ማንሣት እንደሌለባቸው ሊያስተምሩና ግንዛቤ ማስረፅ ይገባቸዋል፡፡

ጨረራ እንደማንኛውም ቁስ በአይን በጆሮ በአፍንጫ የሚለይ ባለመሆኑ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ በተጨማሪም በዓመት የህብረተሰቡን የጨረር ተጋላጭነት ከ1 ሚሊሲቨርት መብለጥ የለበትም፡፡ የጨረራ ሠራተኛ ከሆነ ግን በዓመት የጨረራ ውሰድ መጠን ከ12 ሚሊሲሊቨርት መብለጥ የለበትም፡፡